አንበሳ ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ) ከዚህ በፊት ይጠቀምባቸው የነበሩ ያገለገሉ ኮምፒተር እና ተዛማጅ እቃዎች ፣ ያገለገሉ የቢሮ ማሽኞች፣ ያገለገሉ የቢሮ ፈርኒቸሮች ፣ ያገለገሉ ሶኒ ካሜራዎች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

lion-insurance-Company-logo

Overview

 • Category : Other Sale
 • Posted Date : 02/09/2022
 • Phone Number : 0116187000
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 02/16/2022

Description

አንበሳ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ

ያገለገሉንብረቶችሽያጭግልፅጨረታማስታወቂያቁጥር/001/2014

አንበሳ ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ) ከዚህ በፊት ይጠቀምባቸው የነበሩ ያገለገሉ ኮምፒተር እና ተዛማጅ እቃዎች ፣ ያገለገሉ የቢሮ ማሽኞች፣ ያገለገሉ የቢሮ ፈርኒቸሮች ፣ ያገለገሉ ሶኒ ካሜራዎች ፣ ላፕቶፕ ኮምፒተሮች እንዲሁም ያገለገሉ የውሃ ማጣሪያዎች፣ ታይፕራይተሮች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

በዚህም መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩት የጨረታ ቅድመ ሁኔታዎች እና መስፈርቶች ማሟላት የሚችሉ ተጫራቶች መወዳደር ይችላሉ፡፡

 1. ተጫራቶች የግልፅ ጨረታ ሰነድ ዘውትር በስራ ሰዓት ከሰኞ አስከ አርብ ከ2፡00 -11፡00 እና ቅዳሜ ከ2፡00-6፡00 ሰዓት የማይመለስ ብር 50.00 (ሃምሳ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታ መዝጊያው ቀን ድረስ መግዛት ይችላሉ፡፡
 2. ጨረታው መዝግያ እና መክፈቻ ቀንና ሰዓት የካቲት 9 ቀን 2014 ዓ.ም 3፡30 ተዘግቶ በዚው እለት 4፡00 ላይ የሚከፈት ይሆናል፡፡
 3. ከጨረታው መዝግያ ቀን እና ሰዓት በኋላ የሚቀርብ የመወዳደሪያ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም፡፡
 4. ተጫራቶች ለሚወዳደሩበት ንብረት ለሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 25% በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ሰነድ (CPO) በአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ስም አሰርተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 5. ማንኛውም ተጫራች የሚገዛውን ንብረት አይነት በመጥቀስ በባንኩ የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ሞልቶ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ (ፖስታ) በማድረግ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
 6. የጨረታው መወዳደሪያ ሰነድ ግልፅ እና ሰርዝ ድልዝ እና አሻሚ ያልሆነ መሆን ይኖርበታል፡፡ ስርዝ ድልዝ የተደረገ ዋጋ በፈራሚ አካል ፓራፍ/ኢንሺያል ፊርማ መደረግ ይኖርበታል፡፡
 7. ተጫራቾችን ብረቶቹን ከየካቲት 03 እስከ 06 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00-6፡00 ብቻ አቃቂ ቃሊቲ ወረዳ 05 ጣሳና ቆርኪ ፋብሪካ ገባ ብሎ በሚገኘው የአንበሳ ኢንሹራንስ ሪከቨሪ ውስጥ በሚገኘው የኢንሹራንሱ ንብረት ማከማቻ መጋዝን ቅጥር ግቢ ውስጥ ማየት ይቻላል፡፡
 8. ጨረታው አንበሳ ኢንሹራንስ ኩባንያ ዋናው መ/ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
 9. አሸናፊ ተጫራቶች ለጨረታው ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቶች ደግሞ የጨረታው ውጤት ከተገለፀ በ3 ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል ፡፡
 10. በጨረታው ከፍተኛ ዋጋ ያቀረበ ተጫራቶች አሸናፊ ሆኖ ይመረጣል፡፡ ሁለት ወይም ከዚያ በላይ ተጫራቶች ለተመሳሳይ እቃ እኩል ዋጋ ቢያቀርቡ በእለቱ ውድድር አድርገው ከፍተኛ ዋጋ ያቀረበው ተጫራች አሸናፊ ሆኖ ይመረጣል፡፡ አዲስ ያቀረበው ዋጋም የመጨረሻ ዋጋ ሆኖ ይመዘገብለታል፡፡
 11. በኢንሹራንሱ ሰራተኞች እና በተጨራቶች መካከል ውድድርን ሊገድብ የሚችል የጥቅም ግጭት እንዳለ የሚያሳይ አጠራጠሪ ሁኔታ መኖሩ ከተረጋገጠና ጨረታውን ለመሰረዝ የሚያስገድድ ሁኔታ ከተፈጠረ ጨረታው ሊሰረዝ ይችላል፡፡
 12. በጨረታው አንድ ተጫራች ብቻ ዋጋ ካቀረበ እና የቀረበው ዋጋ የገበያ ዋጋ አለመሆኑን ካመነበት ኢንሹራንሱ ጨረታውን ሊሰርዘው ይችላል፡፡
 13. አሸናፊ ተጫራቶች ማሸነፋቸው በኩባንያው ማስታወቂያ ሰሌዳ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ5 የሥራ ቀናት ውስጥ ገንዘቡን ለኢንሹራንሱ ከፍለው ንብረቱን በ7 ቀናት ውስጥ መረከብና ማንሳት ይኖርባቸዋል፡፡
 14. በተባለው ጊዜ ክፍያው ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረክበው ያልወሰዱ ተጫራቶች ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ /ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ለኩባንያው ገቢ ሆኖ ንብረቱ በድጋሚ ይቀርባል፡፡
 15. አሸናፊው ድርጅት አሸናፊ የሆነባቸውን ዕቃዎች በራሱ ወጪ የማስጫን እና የማገጓጓዝ ሀላፊነት አለበት፡፡
 16. አሸናፊ ተጫራቶች ለተጫረቱበት ንብረት ተጨማሪ እሴት ታክስ ይከፍላሉ፡፡
 17. ተጫራቾች ንብረቶቹን በሙሉ ወይም በከፊል መጫረት ይችላሉ፡፡
 18. ስለ እያንሳነዱ ንብረት ዝርዝር እና ሌሎቸ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት አንበሳ ኢንሹራን ስኩባንያ (አ.ማ) ዋናው መ/ቤት በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 011-6-18 70 00 ማግኘት ይችላል፡፡
 19. ኢንሹራንሱ ስለንብረቶቹ አሻሻጥ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ ሃይሌ ገ/ስላሴ ጎዳና ( ዘሪሁን ህንፃ ጎን)

ስ.ቁ 011-6-18-70-00 / 011-6-62-37-85