ክራይ ቤት ይብቃ የመኖርያ ህብረት ስራ ማህበር ላሰራው B+G+6 ህንፃ ሊፍት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
Overview
- Category : Machinery Purchase
- Posted Date : 02/13/2022
- Phone Number : 0911529442
- Source : Reporter
- Closing Date : 03/01/2022
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
ክራይ ቤት ይብቃ የመኖርያ ህብረት ስራ ማህበር ላሰራው B+G+6 ህንፃ ሊፍት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ፡-
- ህጋዊና የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላችው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ከጽ/ቤታችን ለዚህ የተዘጋጀውን ዶክሜንት መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የሚወዳደሩበትን ዝርዝር ዋጋ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቪሎፕ ማስታወቂያው ከወጣበት እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ አራት ሰዓት /4፡00/ድረስ ለዚሁ ግዥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ በ4፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ፣ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ለመወዳደር ካቀረቡት ጠቅላላ ዋጋ 2% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ /CPO/ ክጨረታ ዶክመንት ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ለጨረታው የሚቀርበው ሊፍት ትክክለኛና /ኦርጂናል/ መሆን አለበት፡፡
- ጨረታውን ያሸነፈ ተወዳዳሪ አሸናፊነቱ በደብዳቤ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ እስከ ሰባት ቀን ድረስ ውል መዋዋል አለባቸው፡፡ ከዚህ ቀን በኋላ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ገንዘብ ለጽህፈት ቤቱ ገቢ ይሆናል፡፡
- ማህበሩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- ገርጂ መብራት ሃይል አካባቢ ፡ ወደ እግዚአብሄር አብ በሚወስደው መንገድ ጫፍ ላይ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0911529442 መጠየቅ ይቻላል፡፡
ክራይ ቤት ይብቃ የመኖርያ ህብረት ስራ ማህበር