ፍቅር ኢትዮጵያ የአዕምሮ ዕድገት ውስንነት ብሔራዊ ማህበር ከኤን.ኤፍ.ዩ ጋር በመተባበር ለሚያሰራው የአዕምሮ ዕድገት ውስንነትን የተመለከተ ማሰልጠኛ መምሪያ ለማሰራት ይፈልጋል

Overview

 • Category : Education & Training Services
 • Posted Date : 02/11/2022
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 02/18/2022

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ፍቅር ኢትዮጵያ የአዕምሮ ዕድገት ውስንነት ብሔራዊ ማህበር ከኤን.ኤፍ.ዩ ጋር በመተባበር ለሚያሰራው የአዕምሮ ዕድገት ውስንነትን የተመለከተ ማሰልጠኛ መምሪያ ለማሰራት የወጣ ጨረታ

ተፈላጊ መስፈርቶች

 1. ያለው ት/ት መረጃ በዚህ ዙሪያና ተያያዥ የት/ት መስኮች የሆነ
 2. በአዕምሮ እድገት ውስንነት ዙሪያ የሰራና ተመሳሳይ መመሪያዎችን ያዘጋጀ
 3. ቫት ተመዝጋቢ የሆነና የታደሰ የስራ ፍቃድ ያለው

የማሰልጠኛ መምሪያው ይዘት

 1. የአእምሮ እድገት ውስንነት ትርጎሜ
 2. የአእምሮ እድገት ውስንነት ምክንያቶች/መንስኤዎች ምን ምን ናቸው
 3. የአእምሮ እድገት ውስንነት ደረጃዎች
 4. የአእምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸው
  • አካላሚ እድገት
  • ማኅበራዊ እድገት
  • ስሜታዊ እድገት
  • ባህሪያዊ እድገት
  • ንግግራዊ /ተግባቦታዊ እድገት እና
  • ከትምህርት ጋር የተያያዙ መገለጫዎች ምንድን ናቸው
 1. የአእምሮ እድገት ዋና ዋና የልየታ እና ምዘና ዘዴዎች
 2. ለአእምሮ እድገት ውስንነት ተጋላጭ የማህበረሰብ ክፍሎች የሚሰጡ ድጋፍ፣ እንክብካቤ እና ህክምና ዓይነቶች
 3. የአእምሮ እድገት ውስንነት ላለባቸው የማህበረሰ ክፍሎች የሚደረግ እገዛ
  • የወላጆች/ቤተሰብ ሚና
  • የት/ት፣የስልጠና የማህበራዊ ዘርፍ ተቋማት ሚና
  • የመምህራን እና የባለሞያዎች ሚና
 1. የአእምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸው ሰዎች ሁለተናዊ እድገት ማበልፀጊያ (ማስተማሪያ ወይም ማሰልጠኛ) ዘዴዎች ወይም ስልቶች
  • የአእምሮ እድገት ውስንነት ስርአተ ትምህርት/ስልጠና ዓላማ
  • የአእምሮ እድገት ውስንነት ትምህርት/ስልጠና ይዘቶች
  • ጨረታውን እስከ አርብ የካቲት 11 ቀን 2014 ዓ.ም ይዘጋል
  • ጨረታው በከፊልም ሆነ በሙሉ ከጨረታ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

ማሳሰቢያ

ይህ መምሪያ ውል በተፈፀመ አካል በ20 ቀናት ውስጥ ተጠናቆ ለማህበሩ መረከብ ይኖርበታል፡፡