የኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ አ.ማ እና በቢፍቱ ባቱ ዩኒየን ብድርና ቁጠባ ተቋም መካከል በዩኒየኑ ስም ተመዝግቦ የሚገኘዉን አክሲዮን ድርሻ በግልጽ ጫረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
Overview
- Category : Bank Related
- Posted Date : 02/11/2022
- Source : Reporter
- Closing Date : 03/01/2022
Description
የኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ አ.ማ እና በቢፍቱ ባቱ ዩኒየን ብድርና ቁጠባ ተቋም መካከል ባለዉ የፍርድ አፈጻጸም ክስ ምክንያት የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ምስራቅ ምድብ ችሎት በኮ/መ/ቁ 373777 ላይ በ18/05/2014 ዓ.ም በዋለዉ ችሎት በፍ/ባለዕዳ ቢፍቱ ባቱ ዩኒየን ስም ተመዝግቦ በኦሮሚያ ሕብረት ሥራ ባንክ አ.ማ የሚገኘዉ የአክሲዮን ድርሻ ተሸጦ ለፍ/ቤቱ ሪፖርት አንዲደረግ አዟል፡፡ በዚሁ መሰረት ባንኩ በዩኒየኑ ስም ተመዝግቦ የሚገኘዉን አክሲዮን ድርሻ በግልጽ ጫረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ተጫራቾች ለጫረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች አንብቦ በመገንዘብ ማክበር ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታውን በድርጅት ስም የሚጫረት ተጫራች በዘመኑ የታደሰ የንግድ ምዝገባ ወረቀት፣ የንግድ ፍቃድና ከድርጅቱ የተሰጠዉ ውክልና መቅረብ አለበት::
- ተጫራቾች ጨረታው በሚካሄድበት ዕለት የጨረታውን መነሻ ዋጋ ¼ (25%) የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ በባንክ ክፍያ ማዘዣ ሲፒኦ በኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ አ.ማ ስም አሰርተው በመቅረብ ተመዝግበዉ ጨረታዉ ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡፡ ጨረታዉ ከታች በተገለጸዉ ቀን በባንኩ ዋና መ/ቤት ቦሌ መንገድ ፍላሚንጎ ጌት ሀዉስ ህንጻ ላይ 5ኛ ፎቆ ላይ ይከናወናል፡፡
- ጨረታው ከታች ቀንና ሰዓቱ በተገለጸው መሠረት ባለዕዳዎች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ለጨረታ የቀረቡት ንብረቶች በሚገኙበት ቦታ ይካሄዳል፤ ባለዕዳዎች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ሳይገኙ ቢቀሩ ግን ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል፡፡
- ተጫራቾች ኢትዮጵያዊ ዜግነት ወይም ትዉልደ ኢትዮጵያዊ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ይዘዉ መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ5 (አምስት ቀናት) ውስጥ አጠቃሎ መክፈል አለበት፤ በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ግን ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ተሰርዞ አዲስ የሐራጅ ማስታወቅያ ወጥቶ የሚካሄድ ይሆናል፡፡
- በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲፒኦ ወይንም ጥሬ ገንዘብ ወዲያውኑ ተመላሽ ይደረጋል::
- የጨረታው አሸናፊ በሕጉ መሠረት የሚከፈለውን ማናቸውንም ክፍያና የስም ማዛወሪያ ከፍሎ ስሙን ወደ እራሱ ያዛውራል፡፡
- ባንኩ የተሸለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ተ.ቁ | ለጨረታ የቀረበዉ ንብረት አይነት | የአክሲዮን መለያ ቁጥሩ | የአክሲዮን ብዛት | የአንዱ እክሲዮን መነሻ ዋጋ | ጠቅላላ የአክሲዮኑ መነሻ ዋጋ | የጨረታዉ መክፈቻ ቀንና ሰዓት አንዲሁም ጊዜ | ||
ቀን | ሰዓት | ጨረታዉ የወጣዉ | ||||||
1 | አክሲዮን | 0006223 | 8556 | 100 | 855,600.00 | የካቲት 22 ቀን 2014 ዓ.ም | ከጠዋቱ 3፡00- 6፡00 | ለሁለተኛ ጊዜ |
የኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ አ.ማ