ሲጂኤፍ ቆርኪ ማምረቻ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ተረፈ ምርቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
Overview
- Category : Disposal Sale
- Posted Date : 02/12/2022
- Phone Number : 0114622066
- Source : Reporter
- Closing Date : 02/18/2022
Description
ሲጂኤፍ ቆርኪ ማምረቻ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
CGF CROWN CORK MANUFACTURING PLC
የተረፈ ምርት የጨረታ ማስታወቂያ
ሲጂኤፍ ቆርኪ ማምረቻ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ተረፈ ምርቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለጸው ዝርዝር መሰረት የመጫረቻ ዋጋቸውን በሰም በታሸገ ፖስታ ከ የካቲት 07/ 2014 ዓ.ም እስከ የካቲት 17 /2014 ዓ.ም ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ጎተራ ባለኬር ህንጻ 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 605 በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ማስገባት የሚችሉ ሲሆን ተረፈምርቱንም ሰንዳፋ በሚገኘው ሲጂኤፍ ቆርኪ ማምረቻ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ፋብሪካ ቅጥር ጊቢ ውስጥ ከየካቲት 07 / 2014 ዓ.ም እስከ የካቲት 11/ 2014 ዓ.ም ድረስ አዲስ አበባ በሚገኘው ቢሮ በመቅረብ የቀጠሮ ሰአት በማስያዝ መመልከት ይችላሉ ፡፡
ቁጥር | ተረፈ ምርት አይነት | ተረፈ ምርት የሚገኝበት ቦታ | መለኪያ | የጨረታ ሁኔታ |
1 | የላሜራ ተረፈ ምርት sheet (Skeleton) | ሰንዳፋ | በኪሎ ግራም | በየ 3 ወር (ለ3 ወር ቋሚ ዋጋ መቅረብ አለበት ) |
2 | የተበላሸ ላሜራ ህትመቱን በማጥፋት | ሰንዳፋ | በኪሎ ግራም | በየ 3 ወር (ለ3 ወር ቋሚ ዋጋ መቅረብ አለበት ) |
3 | የላሜራ ሽፋን | ሰንዳፋ | በኪሎ ግራም | በየ 3 ወር (ለ3 ወር ቋሚ ዋጋ መቅረብ አለበት ) |
4 | የብረት ቦንዳ | ሰንዳፋ | በኪሎ ግራም | በየ 3 ወር (ለ3 ወር ቋሚ ዋጋ መቅረብ አለበት ) |
5 | የተሰባበሩ ፓሌት ትልቅ እና ትንሽ | ሰንዳፋ | በቁጥር | በየ 3 ወር (ለ3 ወር ቋሚ ዋጋ መቅረብ አለበት ) |
6 | ካርቶን ትልቅ እና ትንሽ | ሰንዳፋ | በቁጥር | በየ 3 ወር (ለ3 ወር ቋሚ ዋጋ መቅረብ አለበት ) |
7 | ፓሊባግ ተረፈ ምርት | ሰንዳፋ | በኪሎ ግራም | በየ 3 ወር (ለ3 ወር ቋሚ ዋጋ መቅረብ አለበት ) |
8 | ፒቪሲ ተረፈ ምርት | ሰንዳፋ | በኪሎ ግራም | በየ 3 ወር (ለ3 ወር ቋሚ ዋጋ መቅረብ አለበት ) |
9 | የተበላሸ ቆርኪ | ሰንዳፋ | በኪሎ ግራም | በየ 3 ወር (ለ3 ወር ቋሚ ዋጋ መቅረብ አለበት ) |
ማሳሰቢያ
- ተጫራቾች ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ፣የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለበት ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ዋጋ በሰም በታሸገ ፖስታ ማስገባት ይኖርባቸዋል ፡፡
- ከአጠቃላይ ተጫራቾች ካስገቡት ዋጋ ከፍተኛ ሆኖ የተገኘው ተጫራች አሸናፊ የሚሆን ሲሆን ፣ ለአሸናፊ ተጫራች በደብዳቤ የሚገለጥ ይሆናል ፡፡
- ድርጅቱ ተረፈ ምርቱን ለማጓጓዝ የሰው ሀይል ሆነ ትራንስፖርት አያቀርብም፡፡
- አሸናፊ ተጫራች ተረፈ ምርቱን ከፋብሪካው በሚሰጠው ደብዳቤ መሰረት በ 3 ቀናት ውስጥ ማናሳት ይኖርበታል ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድቦንድ ) በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ(CPO) 20.000.00 (ሃያ ሺ ) በታሸገ ፖስታ አያይዞ ማቅረብ ይኖርበታል አሸናፊ ላልሆነ አካል ተመላሽ ይሆናል ፡፡
- ድርጅቱ ጨረታውን በከፊል ሆን በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ፡፡
አድራሻ፡ ጎተራ ባለኬር ህንጻ 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 605 አዲስ አበባ ኢትዮጽያ
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር : +251 114 622066 /03 ፋክስ፡-: +251 114 622176