እፎይታ በኮልፌ የገበያ ማዕከል አክሲዮን ማህበር በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ በወረዳ 10 በኮልፌ አጠና ተራ በ7200 ካሬ ሜትር ባረፉ 3 የተለያዩ ብሎኮች ግዙፍ የገበያ ማዕከል ላይ ጥራቱን የጠበቀ የደህነት ካሜራ /Security Camera/ ማቴሪያሉን ጨምሮ ከነገጠማው በባለሙያ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

Overview

  • Category : Machinery
  • Posted Date : 02/12/2022
  • Phone Number : 0930540499
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 03/05/2022

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

እፎይታ በኮልፌ የገበያ ማዕከል አክሲዮን ማህበር በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ በወረዳ 10 በኮልፌ አጠና ተራ በ7200 ካሬ ሜትር ባረፉ 3 የተለያዩ ብሎኮች ግዙፍ የገበያ ማዕከል ላይ ጥራቱን የጠበቀ የደህነት ካሜራ /Security Camera/ ማቴሪያሉን ጨምሮ ከነገጠማው በባለሙያ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም በዘርፉ በቂ ልምድ ያላቸው ድርጅቶች፣ በተመሳሳይ የገበያ ማዕከላት ላይ ስለመስራታችሁ ማስረጃ ማቅረብ የምትችሉ፣ በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድና ዋና ምዝገባ ያላችሁ፣ ቫት ተመዝጋቢ የሆናችሁ ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሰረት ተጫራቾች የገበያ ማዕከሉን በአካል ማየት ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በማህበሩ ስም ብር 30,000.00 /ሰላሳ ሺህ ብር/ በባንክ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

ተጫራቾች ለሥራው ከሶስት ያልበለጡ አማራጮችን /Standards/ ከነዋጋው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ አ/ማህበሩ ጽ/ቤት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች በተናጠል ወይም በአንድ ላይ መወዳደር ይችላሉ፡፡ ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 20 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በማግስቱ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

አ/ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አ/ማህበሩ

ለበለጠ መረጃ፡- በ0118-29 09 91-95 እና 0930-54 04 99 ወይም 0910-42 87 60 እፎይታ በኮልፌ ገበያ ማዕከል አ/ማህበር