የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኀበር ልዩ ልዩ ሞዴል ያላቸውን ያገለገሉ ተሸከርካሪዎችን ባሉበት ቦታ እና ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል ፡፡

Ethiopian-Red-Cross-Society-logo-2

Overview

  • Category : Vehicle Sale
  • Posted Date : 02/12/2022
  • Phone Number : 0115509120
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 03/04/2022

Description

ያገለገሉ ተሸከርካሪዎች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኀበር ልዩ ልዩ ሞዴል ያላቸውን ያገለገሉ ተሸከርካሪዎችን ባሉበት ቦታ እና ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል ፡፡

ተጫራቾች ጨረታው በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት የካቲት 6 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ እስከ የካቲት 22 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ በተከታታይ ባሉት የሥራ ቀናት ጠዋት ከ3፡00-5፡30 እና ከሰዓት በኋላ 7፡30-10፡30 ሰዓት ድረስ ሳሪስ አደይ አበባድርና ማግ ፋብሪካ በስተጀርባ በሚገኘው የማኀበሩ ማዕከላዊ መጋዘንና ጋራዥ በመገኘት መጎብኘት እና  ተጫራቾች ለመግዛት የፈለጉትን ተሸከርካሪ የጨረታ መነሻ ዋጋ መመልከት ይችላሉ፡፡

የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና መጠን በእያንዳንዱ ተሸከርካሪ ላይ የተለጠፈውን በመመልከት የተጠቀሰውን የገንዘብ መጠን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር  (Ethiopian Red Cross Society) ስም በተዘጋጀ CPO ስታዲየም አካባቢ በሚገኘው የማኀበሩ ፋይናንስ መምሪያ ድረስ በመቅረብ እስከ የካቲት 22 ቀን 2014 ዓ.ም  ከቀኑ 10፡30 ድረስ ብቻ በቅድሚያ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል ፡፡

  1. ጨረታው የካቲት 24 እና 25 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ ሳሪስ በሚገኘው የማህበሩ ግቢ ውስጥ ይካሄዳል ፡፡
  2. ማንኛውም ከመንግስት የሚጠየቅ ክፍያ ታክስና ከስም ማዛወር ጋር የተያያዙ ወጪዎችን ገዢ ይሸፍናል፡፡
  3. ተጫራቾች በጨረታ ያሸነፉትን ተሸከርካሪ ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ (100%) በመክፈል በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ መረከብ ይኖርባቸዋል ፡፡ አሸናፊው ተጫራች በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ያሸነፈበትን ዋጋ በሙሉ ከፍሎ ተሸከርካሪውን ካልወሰደ ያስያዘው ገንዘብ ለማኅበሩ ገቢ ተደርጎ አሸናፊነቱ ይሰረዛል ፡፡
  4. ስለጨረታው ተጨማሪ ማብራሪያ ሲፈልጉ ከዚህ በታች በተጠቀሰው አድራሻ ስልክ በመደወል መጠየቅ የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን ፡፡
  5. ማኅበሩ የተሻለ መንገድ ካገኝ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር

ስልክ ቁጥር 0115 50 91 20

  አዲስ አበባ