የኢትዮጵያ ኦርተቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት በ2014 ዓ/ም በጀት ዓመት ለጽ/ቤቱ የሚያስፈልጉ የተዘረዘሩትን ለጽ/ቤታችን አገልግሎት የሚሰጡ ልዩ ልዩ እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
Overview
- Category : Purchases
- Posted Date : 02/12/2022
- Phone Number : 0111565950
- Source : Reporter
- Closing Date : 02/25/2022
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ኦርተቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት በ2014 ዓ/ም በጀት ዓመት ለጽ/ቤቱ የሚያስፈልጉ
- የጽሕፈት መሣሪያዎች
- የጥገና መሣሪያዎች
- የጽዳት ዕቃዎች
- የቧንቧ እቃዎች
- የኤሌትሪክ መሣሪያዎችን ከተራ ቁጥር 1- 5 የተዘረዘሩትን ለጽ/ቤታችን አገልግሎት የሚሰጡ ልዩ ልዩ እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባችኋል፡፡
- የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ እና የዘመኑን ግብር ለመከፈላችሁ መረጃ ማቅረብ የምትችሉ፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ በዕቃ አቅራቢነት በፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ለመመዝገቡ የምስከር ወረቀት እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
- ጨረታውን ለመሳተፍ በቅድሚያ ለተጠቀሱት ዕቃዎች የማይመለስ ብር 100.00 አንድ መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት አምስት ኪሎ በሚገኘው መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት በመቅረብ ከሒሳብ ክፍል መግዛት የምትችሉ መሆኑን
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዶቻቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ከያካቲት 7 እስከ የካቲት 18 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ በጠቅላላ አገልግሎት ዋና ክፍል ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገበት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ለአያንዳንዱ የሚያቀርቡት ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት፡፡
- ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ7 ተከታታይ የሥራ ቀናት ድረስ ይቆያል፡፡ በተጨማሪም ተጫራቾች ባይገኙም የጨረታው ሂደት አይሰተጓጎልም፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ዕቃዎቹን በራሱ ትራንስፖርት ተቋሙ ድረስ በማቅረብ ገቢ ያደርጋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5,000.00 / አምስት ሺህ ብር /በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ በጠቅላይ ቤተ ክህነት ስም ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ጨረታው የካቲት 18 ቀን 2014 ዓ/ም ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ተዘግቶ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የስብከተ ወንጌል አዳራሽ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ድርጅት ማሸነፉ እንደተገለጸለት በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ዕቃውን ማቀረብ አለበት ካላቀረበ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመሥሪያ ቤቱ ገቢ ይሆናል፡፡
- ተወዳዳሪዎች ከላይ ከተራ ቁጥር 1 እስከ 5 የተጠቀሱትን ዕቃዎች ለመግዛት በቀረቡት የዕቃ ዝርዝር መሠረት ለእያንዳንዳቸው የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ለየብቻው በመግዛት መወዳድር ይጠበቅባቸዋል፡፡
- እያንዳንዱ እቃ በየአይነቱ ጥራቱንና ደረጃውን የጠበቀ ኦርጂናል መሆን አለበት፡፡
- ተጫራጮች በውድድሩ ካላሸነፉ ለጨረታ መወዳደሪያ ያስያዙትን ሲፒዮ በአምስት ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ መውሰድ ይጠበቅባቸዋል፡፡
ማሳሰቢያ፡– ጠቅላይ ጽ/ቤቱ የተሸለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 01-11-56-59-50 / 0970630037/ ዘወትር በሥራ ቀን ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡