ሕብረት ባንክ አ.ማ. በቦሌ መድኃኒዓለም እና በሲ ኤም ሲ ቅርንጫፎቹ በኩል ለሰጠው ብድር በመያዣነት የያዛቸውን ከዚህ በታች የተመለከቱትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሠረት በግልጽ ሐራጅ (ጨረታ) አወዳድሮ ይሸጣል፡፡
Overview
- Category : House & Building Foreclosure
- Posted Date : 02/12/2022
- Phone Number : 0115573772
- Source : Reporter
- Closing Date : 03/29/2022
Description
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ማስታወቂያ፤
ሕብረት ባንክ አ.ማ. በቦሌ መድኃኒዓለም እና በሲ ኤም ሲ ቅርንጫፎቹ በኩል ለሰጠው ብድር በመያዣነት የያዛቸውን ከዚህ በታች የተመለከቱትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሠረት በግልጽ ሐራጅ (ጨረታ) አወዳድሮ ይሸጣል፡፡
የቅርንጫፍ ስም | የተበዳሪ ስም | የአስያዥ ስም | ቤቶቹ የሚገኝበት አድራሻና የቦታዉ ስፋት | የይዞታ ልዩ መለያ ቁጥር | የሐራጅ መነሻ ዋጋ በብር | ሐራጁ የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት |
ቦሌ መድኃኒዓለም |
ልዩ ዘገዬ እምሩ |
ልዩ ዘገዬ እምሩ |
አዲስ አበባ ከተማ፣ የካ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 13፣ የቦታው ስፋት 555.05 ካ/ሜ የሆነ ለመኖሪያ አገልግሎት የሚውል፤ |
AA000051302053 |
17,765,314.00 |
መጋቢት 20 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ ከ4፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት |
ሲ ኤም ሲ |
በጥረት ኢንተርናሽናል ኃላ/የተ/የግ/ማህበር |
በጥረት ኢንተርናሽናል ኃላ/የተ/የግ/ማህበር |
አዲስ አበባ ከተማ፣ ቂርቆስ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 02፣ የቤት ቁጥር 190፣ የቦታው ስፋት 951 ካ/ሜ የሆነ ለድርጅት አገልግሎት የሚውል፤ |
AA000040200115 |
16,286,276.00 |
መጋቢት 27 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ ከ4፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት |
የሐራጅ ደንቦች
- ተጫራቾች የሐራጁ መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ.) ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ፡፡ ከባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ) ውጭ የሚቀርብ የጨረታ ማስያዣ ተቀባይነት የለውም፡፡
- አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በአስራ አምስት (15) ቀናት ዉስጥ አጠቃልሎ ካልከፈለ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ ይሰረዛል፡፡ በተጨማሪም ንብረቱ በድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል፡፡
- በሐራጅ ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች፣ ተበዳሪዎች እና አስያዦች ብቻ ናቸው፡፡
- ተጫራቾች በሐራጅ ለመሳተፍ ሲገኙ መታወቂያ መያዝ ይገባቸዋል፡፡ ተጫራቾች የሕግ ሰውነት የተሰጣቸው አካላት ከሆኑ ሕጋዊ ሰውነት ያገኙበት የዋና ምዝገባ ምሥክር ወረቀት እንዲሁም ሐራጁን ለመሳተፍ የቀረበው ሰው ሥልጣኑን የሚያሳይ በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽ/ቤት የፀደቀ መመሥረቻ ጽሑፍ፣ መተዳደሪያ ደንብ፣ ቃለ ጉባኤ ወይም የውክልና ሥልጣን ማስረጃ ይዞ መቅረብ አለበት፡፡
- የሐራጅ ሽያጩ የሚካሄደው የመያዣው ንብረት በሚገኝበት ቦታ ላይ ነው፡፡
- የተጫራቾች ምዝገባ ከሐራጁ መዝጊያ ሰዓት ሰላሳ ደቂቃ በፊት ይጠናቀቃል፡፡ በሐራጁ ሰላሳ (30) ደቂቃዎች የተጫራች ምዝገባ አይካሄድም፡፡
- ለሐራጅ የቀረበውን ንብረት ለመጎብኘት የሚፈልጉ ከሕብረት ባንክ ሕግ አገልግሎ መምሪያ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ ከጨረታው ቀን ሶስት ቀናት አስቀድሞ መጎብኘት ይችላሉ፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ እና ሌሎች ገዥ እንዲከፍላቸው በህግ የተወሰኑ የታክስና ግብር የስም ማዛወሪያ እንዲሁም የሊዝ ክፍያዎችን ጭምር /የጨረታዉ አሸናፊ/ ገዥዉ ይከፍላል፡፡
- ባንኩ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር +251115573772/0114700315/69/47/4103 ሕግ አገልግሎት መምሪያ ወይም +2516625924/26/35 ቦሌ መድኃኒዓለም ቅርንጫፍ እና +2516675639/6478564/65/66 ሲ ኤም ሲ ቅርንጫፍ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ሕብረት ባንክ አ.ማ