ሕብረት ባንክ አ.ማ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዛቸውን ንብረቶች ተበዳሪዎች በገቡት ውል መሠረት ብድሩን ወቅቱን ጠብቀው ባለመክፈላቸው ምክንያት የተረከባቸውን እና ከዚህ በታች የተመለከቱትን ንብረቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

hibret-bank-done-logo-reportertenders-5

Overview

 • Category : House & Building Foreclosure
 • Posted Date : 02/12/2022
 • Phone Number : 0114169757
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 03/02/2022

Description

  ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 006/14

ሕብረት ባንክ አ.ማ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዛቸውን ንብረቶች ተበዳሪዎች በገቡት ውል መሠረት ብድሩን ወቅቱን ጠብቀው ባለመክፈላቸው ምክንያት የተረከባቸውን እና ከዚህ በታች የተመለከቱትን ንብረቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

. የአበዳሪ ቅርንጫፍ የተበዳሪው ስም የቀድሞው የቤቱ/ የንብረቱ ባለቤት የቤቱ /የንብረቱ  ዓይነት የቦታው ስፋት በካሬ ሜትር የባለቤትነት መታወቂያ ቁጥር ቤቱ/ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ የጨረታ መነሻ ዋጋ/ብር  ጨረታው የሚዘጋው እና

የሚከፈተው

የካቲት 24 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 9:00  ተዘግቶ የሚከፈትበት በዚሁ ዕለት ከቀኑ 9:30 ሰዓት

ከተማ ክ/ከተማ /ክልል ቀበሌ የቤት ቁጥር ልዩ ቦታ ወይም ስፍራ
1 ኮልፌ ቅርንጫፍ ወይ. ኤልዳና በኃይሉ ወይ. ኤልዳና በኃይሉ መኖሪያ ቤት ተጨማሪ ሰርቪስ ክፍሎች ያሉት 200 ካ.ሜ BMK/1237/2010 መናገሻ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ኮቦሎ አዲስ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፊት ለፊት ከዋናው መንገድ 150 ሜትር ወደ ውስጥ ገባ ብሎ 1,336,186.00
2 ካቴድራል ቅርንጫፍ አቶ አለማየሁ ማሞ አቶ አለማየሁ ማሞ G+1ለቢሮ አገልግሎት የሚውል ሕንፃ እና መጋዘን የንግድ ቤት የቦታው ስፋት 5,000 ካ.ሜ ሆኖ  መጋዘኑ ያረፈበት 2,732 ካ.ሜ እና 105.9 ካ.ሜ ላይ ያረፈ G+1 የቢሮ ሕንፃ አ=1701/2008 መተማ ገንዳ ውሃ ሰ/ጎንደር 02 አዲስ ገንዳ ውሃ 10,853,483.00
3 መተማ ቅርንጫፍ አቶ ዘውዱ ጠቀሳ አቶ ብርሃኑ አሻግሬ መኖሪያ ቤት 250 ካ.ሜ ብ=522/2007 መተማ ገንዳ ውሃ ሰ/ጎንደር 02 አዲስ ገንዳ ውሃ 914,277.00
4 ሰሚት ኮንደሚኒየም አቶ ይሄነው ይፍረድ አቶ ይልቃል አዱኛ የንግድ ቤት 200 ካ.ሜ 315/2009 ሞጣ ምስ/ጎጃም 01 አዲስ ሞጣ 1,575,477.33
5 ጋምቤላ ቅርንጫፍ አቶ ታረቀኝ አረጋ አቶ ታረቀኝ አረጋ መኖሪያ ቤት 504 ካ.ሜ 241449/2002 ጋምቤላ ጋምቤላ 04 አዲሰ ጋምቤላ 633,075.00
6 ባምባሲ ቅርንጫፍ አቶ ጀማል ካሰው አቶ ጀማል ካሰው መኖሪያ ቤት 353 ካ.ሜ 1871/07 ባምባሲ ባምባሲ 01 አዲሰ ባምባሲ 1,316,855.00

በመሆኑም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተገለትን የጨረታ መመሪያ በመከተል መጫረት ይችላሉ፡-

 1. ንብረቶቹን ለማየት የሚፈልጉ በሚያመቻቸው ጊዜ ከላይ በሠንጠረዡ በተገለጹት አድራሻዎች ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ በሥራ ሰዓት ጠዋት ከ3፡00- 6፡00 ከሰዓት ከ 8፡00-10፡00 ሰዓት በመገኘት ንብረቶቹን ማየት ይቻላል፡፡
 2. የጨረታ መነሻ ዋጋ ¼ ወይንም 25% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ /ሲ.ፒ.ኦ/ በማቅረብ መወዳደር ይቻላል፡፡
 3. አሸናፊ የሚሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ገንዘብ በ10/አስር/ የስራ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ይኖርበታል፣ ባይከፍል ግን ጨረታው ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ አይመለስለትም፣ ሆኖም ጨረታውን ላላሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ አሸናፊው ከተለየ በኋላ ይመለስላቸዋል፡፡
 4. ተጫራቾች ንብረቱን የሚገዙበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ንብረት አስተዳደር ዋና ክፍል ሕብር ታወር 4ኛ ፎቅ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ የካቲት 24 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይቻላሉ፡፡
 5. ጨረታው የሚከፈተው የካቲት 24 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 9፡30 ሰዓት በዋናው መስሪያ ቤት የቦርድ መሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
 6. ንብረቱን በገዥው ስም ለማዛወር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ማረጋገጫ ይጽፋል፡፡
 7. ንብረቱን ሙሉ በሙሉ በጥሬ ገንዘብ ከፍለው ለሚገዙ ባንኩ ቅድሚያ የሚሰጥ ቢሆንም እንዳስፈላጊነቱ በባንኩ የብድር ፖሊሲ መሠረት ንብረቱን በብድር ለመግዛት ለሚፈልጉም ንብረቱን የገዙበት (ጨረታውን ያሸነፉበትን) ዋጋ 50% ድረስ ብድር ሊያመቻች ይችላል፡፡ ሆኖም ግን ብድር ለመጠየቅ የሚፈልጉ ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነድ ከማስገቢያው 3/ሶስት/ቀናት በፊት ማለትም የካቲት 21 ቀን 2014 ዓ.ም. በፊት የብድር ጥያቄያቸውን ለባንኩ የብድር እና ትንተና መምሪያ በማቅረብ ብድር ለማግኘት የሚችሉ ስለመሆኑ ማረጋገጫ ማግኘት ይኖርባቸዋል፡፡
 8. ተጨማሪ እሴት ታክስ እና ሌሎች ገዥ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ታክስና ግብሮችን እንዲሁም የስም ማዘዋወሪያ ገዥው/አሸናፊው ይከፍላል፡፡
 9. የንግድ ቤት/ንብረት ለሆኑት ንብረቶች ተወዳዳሪዎች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተ.እ.ታን የሚያካትት ወይም የማያካትት ስለመሆኑ በመጫረቻ ሰነዱ ላይ በግልፅ መስፈር አለበት፡፡
 • ለበለጠ ማብራሪያ ሕብረት ባንክ አ.ማ ዋናው መስሪያ ቤት በስልክ ቁጥር 0114-169757 ወይም 0114- 700315 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡ ወይም ንብረቶቹ በሚገኙበት በመተማ ከተማ መተማ ቅርንጫፍ፤ባምባሲ ከተማ ባምባሲ ቅርንጫፍ፤ሞጣ ከተማ ሞጣ ቅርንጫፍ፣ጋምቤላ ከተማ ጋምቤላ ቅርንጫፍ እና ሆለታ ከተማ ሆለታ ቅርንጫፍ በአካል በመገኘት የሚፈልጉትን መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
 • ባንኩ ንብረቱን ለመሸጥ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡

ሕብረት ባንክ አማ