“ማቲዎስ ወንዱ – የኢትዮጵያ ካንሠር ሶሳይቲ” የሚለው መጠሪያ ስሙ ከራዕዩ፣ ከተልዕኮውና ዓላማው እንዲሁም በመስራት ላይ ከሚገኛቸው ስራዎች የሚጣጣም መሆኑን ማረጋገጥና አስፈላጊ ከሆነም የሚመጥነው መጠሪያና ሎጎ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

Mathiwos-Wondu-YeEthiopia-cancer-society-logo

Overview

 • Category : Graphic Designs & Printing
 • Posted Date : 02/16/2022
 • Phone Number : 0118122837
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 03/01/2022

Description

ማቲዎስ ወንዱ – የኢትዮጵያ ካንሠር ሶሳይቲ ሚያዝያ 9 ቀን 1996 ዓ.ም ተቋቁሞ መጋቢት 12 ቀን 2008 ዓ.ም በበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ኤጀንሲ ዳግም ተመዝግቦና ፈቃድ አግኝቶ በመሥራት ላይ ያለ ለትርፍ ያልተቋቋመ መንግስታዊ ያልሆነ ሀገር በቀል ድርጅት ነው፡፡

ሶሳይቲያችን “ማቲዎስ ወንዱ – የኢትዮጵያ ካንሠር ሶሳይቲ” የሚለው መጠሪያ ስሙ ከራዕዩ፣ ከተልዕኮውና ዓላማው እንዲሁም በመስራት ላይ ከሚገኛቸው ስራዎች የሚጣጣም መሆኑን ማረጋገጥና አስፈላጊ ከሆነም የሚመጥነው መጠሪያና ሎጎ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስምና ሎጎው የሶሳይቲውን ስራዎች፣ አበርክቶዎች፣ በ17 አመታት ቆይታው ያለፈባቸውን መንገዶች፣ አሁን የደረሰበትን ደረጃና የወደፊት ዕቅዶቹን ከግምት ውስጥ ያስገባ እንዲሁም የሶሳይቲውን አጋሮችና የያገባናል ባዮችን አስተያየት የጠበቀና ሶሳይቲውን የሚመጥን መሆን ይኖርበታል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ አመልካቾች የተያያዘውን መነሻ ሰነድ በመመልከት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

 1. ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው/ት፣
 2. በሙያ ብቃትና ፈጠራ በቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የተመዘገበና ከዚህ በፊት ተመሳሳይ ስራ የሰራና ተቀባይነት ያገኘ የሎጎ ሥራ መስራቱን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችልና ሕጋዊ የሆነ/ች፤
 3. የዘመኑን ግብር ከፍለ በ2014 በጀት ዓመት ፈቃድ ያሳደሰ/ች፣
 4. በተመሳሳይ ስራና በሎጎ ዴዛይን ሥራ በቂ የሥራ ልምድና ክህሎት ያለው/ት፣
 5. የታክስ መለያ ቁጥር (Tin Number) ያለው/ት፣
 6. ከአሁን በፊት የሰራውን ስራና የተመዘገበ ሎጎ ማቅረብ የሚችልና እንዲሁም በሃገሪቱ ሕግና መመሪያ መሠረት መስራት የሚችልና በአጭር ጊዜና ተመጣጣኝ በሆነ ዋጋ ለመስራትና ለማቅረብ ፈቃደኛ የሆነ መወዳደር ይችላል/ትችላለች፡፡

ተወዳዳሪዎች ለአገልግሎቱ የምታስከፍሉትን ዋጋ ከነቫቱ እንዲሁም ሥራውን ሠርታችሁ የምታስረክቡበትን ጊዜ የሚገልፅ ማስረጃና ሰነዱን በማያያዝ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከዚህ በታች በተጠቀሰው አድራሻ ለሶሳይቲያችን እንድታመለክቱ እናስታውቃለን፡፡

አድራሻ

ማቲዎስ ወንዱ – የኢትዮጵያ ካንሠር ሶሳይቲ መገናኛ የቀድሞው ካርተር ሴንተር የቤት ቁጥር 156ለ ሲድራ ኢንተርናሽናል ሆቴል ጀርባ ወይም በፓኖራማ ሆቴል መንገድ በችግኝ መሸጫው በአዲሱ መንገድ 200ሜትር ገባ ብሎ

የስልክ ቁጥር 011 8122838 ፣ 0911 48 95 04

ፖ.ሣ.ቁጥር 80571

ኢ-ሜይል – lemmaa@mathiwos.org or

ዌብ ሳይት – www.mathiwos.org

አዲስ አበባ

ኢትዮጵያ