ተስፋ ብርሃን ህፃናትና ቤተሰብ ልማት ድርጅት የጦርነት ውድመት ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸውን የህብረተሰብ ክፍሎችና ተቋማት የመልሶ ማልማት እና ማቋቋም ሥራ ማከናወን ይቻል ዘንድ የሚከተሉትን እቃዎችበጨረታ አወዳድሮ ለማሰራትና ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

Tesfa-Berhan-Child-and-Family-Development-Organization-logo

Overview

  • Category : Purchases
  • Posted Date : 02/16/2022
  • E-mail : tesfaberhancfdo@gmail.com
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 02/24/2022

Description

ተስፋ ብርሃን ህጻናትና ቤተሰብ ልማት ድርጅት

ለ2ኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

ተስፋ ብርሃን ህፃናትና ቤተሰብ ልማት ድርጅት ከኤስኦኤስ የህፃናት መንደሮች በኢትዮጲያ ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ በአማራ ክልል በሚንቀሳቀስባቸው ወረዳዎች በደረሰው የጦርነት ውድመት ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸውን የህብረተሰብ ክፍሎችና ተቋማት የመልሶ ማልማት እና ማቋቋም ሥራ ማከናወን ይቻል ዘንድ የሚከተሉትን እቃዎችበጨረታ አወዳድሮ ለማሰራትና ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ የሚገዛውም

መደብ 1. ላብቶፕ ኮምፒዩተር እና ሌሎች የቢሮ እቃዎች

መደብ 2. ጥራቱን የጠበቀ የስንዴ ዱቄት እና ዘይት

መደብ 3. የመስክና የጭነት መኪና ኪራይ

መደብ 4. የቤት ክዳን ቆርቆሮና ሚስማር

በመሆኑም በመስኩ ልምዱ ያላችሁና በሥራው ለመሳተፍ የምትፈልጉ፡-

  • በዘመኑ የታደሰ ፍቃድ
  • የቫት ምዝገባ ሰርተፍኬት እና
  • የመልካም ሥራ አፈፃፀም የሚያቀርብ

ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ ቀናት እና ሰአት ከድርጅቱ ዋና ጽ/ቤት ቀይት እያንዳንዱን ሰነድ በማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) ብቻ የጨረታ ሰነዱ በመግዛት በኢሜይል አድራሻ tesfaberhancfdo@gmail.com በመጠየቅ እና የጨረታ ሰነዱን ዋጋ በባንክ በማስገባትና  እና የጨረታ ዝርዝሩን ከጨረታ ሰነዱ በማየት ና በመሙላት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ዋናውንና ኮፒን ማስገባት ፡፡

ተጫራጮች የሞሉትን የጠቅላላ ዋጋውን 1% በባንክ ሲፒኦ በድርጅቱ ስም በማሰራት ማስያዝ አለባቸው፡፡ ጨረታው በ8ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰአት ተዘግቶ በ5፡00 ሰአት ጨረታውን ለመካፈል በተገኙ ተጫራቾች እና ወኪሎች ፊት ይከፈታል፡፡ 8ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰአት ተዘግቶ ይከፈታል፡፡ ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው አይገደድም፡፡

ተስፋ ብርሃን ህፃናትና ቤተሰብ ልማት ድርጅት