የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለድሬድዋ አፓርትመንት ፕሮጀክት ግንባታ አገልግሎት የሚውሉ ዝርዝራቸው ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘ የሥራ ዝርዝር (Specification) መሰረት የተለያየ ዓይነት የPPR Pipe & Fittings ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
Overview
- Category : Purchases
- Posted Date : 02/16/2022
- E-mail : INFO@dce-et.com
- Phone Number : 0114403434
- Source : Reporter
- Closing Date : 03/03/2022
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር DCE/SM/10/2022
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለድሬድዋ አፓርትመንት ፕሮጀክት ግንባታ አገልግሎት የሚውሉ ዝርዝራቸው ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘ የሥራ ዝርዝር (Specification) መሰረት የተለያየ ዓይነት የPPR Pipe & Fittings ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ፡-
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩ፤ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚያቀርቡት ገንዘብ በተጫራቾች መመሪያ ተራ ቁጥር 7.3 እና 7.4 በተጠቀሰው መሰረት መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ወሎ ሰፈር አካባቢ በሚገኘው የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ዋናው መ/ቤት የግዥ ሥራ ሂደት ኬዝ ቲም ቢሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸው እቃዎች ኦርጅናል ወይም የድርጅቱ ማህተም ያረፈበት ኮፒ ካታሎግ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ወይም በጨረታ መክፈቻ ቀን በካታሎጉ ላይ የሚወዳደሩበትን ዕቃ ለይቶ በማመልከት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- እንዲሁም በቴክኒካል ሰነድ ማጠቃለያ ሠንጠረዥ ላይ ለሚወዳደሩበት ማቴሪያል የሚያቀርቡት እቃ ተመጣጣኝ ወይም (Equivalent) ከሆነ በግልፅ ተለይቶ መቀመጥ ይኖርበታል፡፡
- ናሙናን በተመከተ ባቀረቡት ካታሎግ መሠረት እና በዋጋቸው የሚመረጡ ተጫራቾች ናሙና እንዲያቀርቡ ሲጠየቁ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡
- ሆኖም ከላይ መሟላት እንዳለበት ከተጠቀሱት ነጥቦች አንዱም ቢጐድል ተጫራቹ ቴክኒካል መስፈርቱን እንዳላሟላ ተቆጥሮ ሠነዱ ተመላሽ ይደረግለታል፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ የካቲት 24/2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው የካቲት 24 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡– የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ
የቀጥታ ስልክ ቁጥር 0114-40-34-34/33
ማዞሪያ 0114-42-22-70/71/72
ፖ.ሳ.ቁ 3414 ፋክስ ቁ. 0114-40-04-71/0114-42-07-46
ወሎ ሰፈር የቀድሞው ኖሬላ ግቢ
www.dce-et.com / Email:- info@dce-et.com