ዋልታ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ኮርፖሬት ለሚያስገነባው ሁለገብ ህንፃ ግንባታ የዲዛይን እና የማማከር አገልግሎት አቅራቢ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል፡፡

Walta-Communications-logo-Reportertenders

Overview

 • Category : Baseline Consultancy
 • Posted Date : 02/20/2022
 • Phone Number : 0114670319
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 03/02/2022

Description

የግንባታ ዲዛይን እና አማካሪ ግልፅ ጨረታ

የጨረታ መለያ ቁ.ዋ/ሚ/ኮ 084/2014

ዋልታ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ኮርፖሬት ለሚያስገነባው ሁለገብ ህንፃ ግንባታ የዲዛይን እና የማማከር አገልግሎት አቅራቢ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተወዳዳሪዎች የጨረታ ሰነዱን በዋናው መስሪያ ቤት የግዥና አቅርቦት ዋና ክፍል በመቅረብ የማይመለስ 200.00 ብር በመክፈል የጨረታ ሰነድ መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

የጨረታው ተወዳዳሪዎች፡-

 • በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚንስቴር በዘርፉ የብቃት ማረጋገጫ ያላቸዉ፣
 • በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች ዉስጥ ደረጃቸው CAT-1 እና በላይ የሆኑ፣
 • ህጋዊና የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣
 • ቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልፅ ሰነድ ማቅረብ የሚችሉ፣
 • የመልካም ስራ አፈፃፀም በጨረታ ሰነዱ በተመለከተው ልክ ማቅረብ የሚችሉ፣
 • ስራዉን ሰርቶ ለማጠናቀቅ የሚወስደዉ ጊዜ በቴክኒካል ሰነዱ ላይ በቀናት ተጠቅሶ በደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ፣
 • የጨረታ ማስካበሪያ ብር 15,000 በሲፒኦ ማስያዝ የሚችሉ፣
 • ተጨማሪ ለውድድሩ የሚጠቅሙ አስፈላጊ ሰነዶችን ማሟላት የሚችሉ ሊሆኑ ይገባል፡፡

ተወዳዳሪዎች የሚያቀርቡት የቴክኒክ መወዳደሪያ አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ እንዲሁም ፋይናንሻል ፕሮፓዛል (ዋጋ ማቅረቢያ) አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ በጨረታው ሰነዱ የተመለከተውን በጥንቃቄ በመከተል፣ በተለያየ ኤንቨሎፕ (ፓስታ) በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

ስለሆነም ተጫራቾች ይህ ጨረታ ለመጀመሪያ ጊዜ በዚህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን 08/06/2014ዓ.ም ጀምሮ እስከ 23/06/2014 ዓ.ም ድረስ የጨረታውን ሰነድ በመሙላት በዋልታ የግዥና አቅርቦት ዋና ክፍል ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ጨረታው በ23/06//2014 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ዋልታ ጨረታውን በሙሉም ይሁን በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ

 • በቅሎ ቤት ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጠመንጃ ያዥ ቅርንጫፍ በስተጀርባ
 • ለበለጠ መረጃ ስልክ በስልክ ቁጥር 0114670319 መደወል ይችላሉ፡፡