አዲስ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ ለሰጠው ብድር ማካካሻ በአዋጅ ቁጥር 97/90 በተሰጠው ስልጣን መሠረት የተረከበውን ከዚህ በታች በሠንጠረዥ የተመለከተውን ቤት በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

Addis-International-Bank-logo-reportertenders-1

Overview

 • Category : House & Building Foreclosure
 • Posted Date : 02/19/2022
 • Phone Number : 0115570509
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 03/09/2022

Description

አዲስ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ

የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

አዲስ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ ለሰጠው ብድር ማካካሻ በአዋጅ ቁጥር 97/90 በተሰጠው ስልጣን መሠረት የተረከበውን ከዚህ በታች በሠንጠረዥ የተመለከተውን ቤት በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡በዚሁ መሰረት ተጫራቾች  ጨረታው በሚካሄድበት ቀን ቤቱ የሚገኝበት ቦታ በመገኘት  መጫረት ይችላሉ፡፡

 

ተ.ቁ

 

አበዳሪው ቅርንጫፍ

ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ  

የቦታ ስፋት

የንብረቱ ዓይነት የጨረታ መነሻ ዋጋ ብር ጨረታው የሚከናወንበት ቀንና ሰዓት
ከተማ ክ/ከተማ
1 ቦሌ መድሃኒ ዓለም አዲስ አበባ  አብነት 339 ካሬሜ. መኖሪያ ቤት 4,700,000.00 የካቲት 30 ቀን 2014ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00-6፡00

ማሳሰቢያ ፡-

 1. ቤቱን ለማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች የካቲት 21፤25 እና 28 ቀን 2014ዓ.ም አዲስ ኢንተርናሽናል ዋና መ/ቤት በሚገኝበት ዝቋላ ኮምፕሌክስ አንደኛ ፎቅ ፋሲሊቲ አስተዳደር ዋና ክፍል በተገለፁት ቀናቶች ብቻ ጠዋት 3፡00 ሰዓት ላይ በመገኘት ንብረቱ የሚገኝበትን ቦታ ማየት ይቻላል፡፡ስልክ ቁጥር 0115 5705 09
 2. የጨረታው ማስከበሪያ የጨረታ መነሻ  ዋጋ ¼ ወይም 25 % በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ /ሲ.ፒ.ኦ/ በጨረታው ዕለት ይዞ በመምጣት መወዳደር ይቻላል፡፡
 3. አሸናፊ የሚሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ገንዘብ በ15 /አስራ አምስት/ ተካታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ይኖርበታል ፡፡ ጨረታውን ላላሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት የክፍያ ሰነድ አሸናፊው ከተለየ በኋላ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፡፡
 4. ጨረታው የካቲት30 ቀን 2014 ዓ.ም  ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ጀምሮ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቤቶቹ ባሉበት ቦታ ይከናወናል፡፡
 5. ንብረቱ በገዥው ስም እንዲዘዋወር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይፅፋል፡፡
 6. በንብረት ማስተላለፍ ሂደት ለመንግስት የሚከፈል ክፍያ ማለትም ታክስ ፣ ግብር ፣ ወይም ሌላ ማንኛውም ክፍያ ገዥው ይከፍላል፡፡
 7. ለበለጠ ማብራሪያ አዲስ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ ዋና መ/ቤት በስልክ ቁጥር 0115 570509/0115 570319 ደውሎ መረዳት ይቻላል፡፡
 8. ባንኩ ንብረቱን ለመሸጥ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ፡፡

አዲስ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ