ብርሃን ኢንሹራንስ አ.ማ የካሣ ክፍያ ፈፅሞ የተረከባቸውን ቀላል የተጎዱ ተሽከርካሪዎች፣ የተለያዩ የተሽከረካሪ መለዋወጫዎች ከዚህ በታች ባለው ዝርዝር መሰረት ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

Berhan-Insurance-logo

Overview

 • Category : Vehicle Sale
 • Posted Date : 02/19/2022
 • Phone Number : 0114674423
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 03/07/2022

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ብርሃን ኢንሹራንስ አ.ማ የካሣ ክፍያ ፈፅሞ የተረከባቸውን ቀላል የተጎዱ ተሽከርካሪዎች፣ የተለያዩ የተሽከረካሪ መለዋወጫዎች ከዚህ በታች ባለው ዝርዝር መሰረት ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

 1. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ጨረታው እስከ ሚያበቃበት ቀን ድረስ ከዋናው መስሪያ ቤት መግዛት ይችላሉ፡፡
 2. ንብረቶቹን ባሉበት ሁኔታ በብርሃን ኢንሹራንስ አ.ማ የተጎዱ ንብረቶች ማከማቻ ቦታ አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 7 ልዩ ቦታው ቃሊቲ 4ዐ/60 ኮንደሚኒየም በኩል ገባ ብሎ በተለምዶ የቆላ ዝንብ አካባቢ (ጨሬ ሰፈር) የጨረታ ሰነድ የገዙበትን ደረሰኝ በመያዝ ንብረቶቹን መመልከት ይችላሉ፡፡
 3. በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ለመጫረት የሚፈልገውን የንብረት ዓይነት እና ያቀረበውን የጨረታ ዋጋ ዝርዝር በመግለፅ ፤የጨረታ ማስከበሪያ የንብረቱን የጨረታ መነሻ ዋጋ 15 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ. በብርሃን ኢንሹራንስ አ.ማ. ስም በማስያዝ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ የካቲት 28 ቀን 2ዐ14 ዓ.ም. ድረስ በሥራ ቀናት ብርሃን ኢንሹራንስ አ.ማ. ዋናው መ/ቤት ቂርቆስ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 02 ቦሌ ወሎ ሰፈር ጋራድ ሲቲ ሴንተር 7 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 7 በአካል በመገኘት የጨረታ ሰነዱን በሰም በታሸገ ፓስታ ለሚጫረቱበት የዕቃ አይነት ማስገባት ይችላሉ፡፡
 4. በጨረታ ለተሸነፉ ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ. ይመለስላቸዋል፡፡ ለጨረታ አሸናፊዎች ደግሞ ያዝያዙት ገንዘብ ለሚገዙት ተሽከርካሪ ወይም መለዋወጫ ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር ይታሰብላቸዋል፡፡
 5. አሸናፊዎች በጨረታው ላሸነፉት ንብረት ቀሪውን ክፍያ እና 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ አክለው በመክፍል የጨረታው ውጤት ከተገለፀበት ጊዜ ጀምሮ ባሉት 5 የስራ ቀናት ውስጥ እቃዎችን መረከብ ይኖርባቸዋል፡፡ በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ያሸነፉትን ንብረት ከፍለው ካልወሰዱ ኩባንያው ለጨረታ ያስያዙትን ሲፒኦ ገቢ አድርጎ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 6. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስን የሚያጠቃልል መሆኑን በግልጽ ሁኔታ በሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ላይ ካልተገለፀ በስተቀር በቀረበው ዋጋ ላይ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስን ተጨምሮ የሚታሰብ ይሆናል፡፡
 7. ተሽከርካሪዎች በጨረታ እስከተሸጡበት ጊዜ ድረስ የሚፈለግ ግብርና ታክስ ወይም ሌላ ክፍያ የሻጩ ኃላፊነት ይሆናል፡፡
 8. አሸናፊ ተጫራቾች የገዙትን ዕቃ ከሪከቨሪ በራሳቸው ወጪ አስነስተው ይወስዳሉ፡፡
 9. ጨረታው የካቲት 28 ቀን 2014 ዓ.ም. ከቀኑ 800 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን በ 83 ሰዓት ላይ የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ጨረታው በሚከፈትበት ወቅት ከኮሮና ቫይረስ ስርጭት ጋር በተያየዘ መገኘት አይጠበቅባቸውም፡፡
 10. ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0114-67-44-23/46 ወይም 0114-70-40-54 መደወል ይቻላል፡፡