ብርሃን ባንክ በ2014 በጀት ዓመት ለሰራተኞች አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች በሰንጠርዥ የተዘረዘሩትን የተለያዮ የደንብ ልብስ ግዥ ለማከናውን በዘርፉ የተሰማሩ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

Berhan-International-Bank-S.c-logo-2

Overview

 • Category : Textiles/ Fabrics & Wearing
 • Posted Date : 02/19/2022
 • Phone Number : 0116632097
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 03/08/2022

Description

  ብርሃን ባንክ አ.ማ

 የደንብ ልብስ ግዢ ጨረታ

በድጋሚ የወጣ/  አገር አቀፍ ግልፅ ጨረታ

የጨረታ ቁጥር፡ ብባ/ግጨ/ደል/2021/22/18  

 1. ብርሃን ባንክ በ2014 በጀት ዓመት ለሰራተኞች አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች በሰንጠርዥ የተዘረዘሩትን የተለያዮ የደንብ ልብስ ግዥ ለማከናውን በዘርፉ የተሰማሩ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም
ምድብ ቁጥር ዓይነት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና መጠን (ብር)
I ቴትሮን 6000 (የኢንዱንዤያ) ጨርቅ 25,000.00
II የባንኩ ዓርማ የታተመበት ጃኬት 65,000.00
III የሱፍ ካፓርት 20,000.00
  በሁሉንም ምድብ ለመወዳደር ለሚፈልጉ 100,000.00
 1. ተጫራቾች ለዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ! የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ የምስክር ወርቀት እና የታክስ ከፋይነት የምስክር ወርቀት የሚያቀርቡ መሆን አለባቸው፡፡
 2. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በማንኛዉም የብርሃን ባንክ ቅርንጫፍ ክፍያ ፈፅመዉ ደረሰኙን በማቅረብ፣ የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ከሚገኝበት ቦሌ ብራስ ሆስፒታል ፊት ለፊት ከሚገኘዉ ወመሳድኮ ህንፃ 2ተኛ ፎቅ ከፋሲሊቲ አስተዳደር መምሪያ ቢሮ ለጨረታዉ የተዘጋጀዉን ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
 3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የቴክኒክ ሰነድ እና የዋጋ ሰነድ አንድ በዋና እና አንድ በኮፒ በተለያዮ ፓስታ ማቅረብ እንዲሁም ናሙና ማያያዝ አለባቸው፡፡
 4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን እስከ የካቲት 29 ቀን 2014 ዓ.ም. ጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ከሚገኝበት ቦሌ ብራስ ሆስፒታል ፊት ለፊት ከሚገኘዉ ወመሳድኮ ህንፃ 2ተኛ ፎቅ ፋሲሊቲ አስተዳደር መምሪያ ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማሰገባት አለባቸው፡፡
 5. ጨረታው የካቲት 29 ቀን 2014 ዓ.ም. ጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ከሚገኝበት ቦሌ ብራስ ሆስፒታል ፊት ለፊት ከሚገኘዉ ወመሳድኮ ህንፃ 2ተኛ ፎቅ ፋሲሊቲ አስተዳደር መምሪያ ቢሮ ይከፈታል፡፡
 6. ባንኩ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታዉን በከፊል ወይም ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብት አለው፡፡

  ብርሃን ባንክ አ.ማ.

ፋሲሊቲ አስተዳደር መምሪያ

ሰልክ ቁጥር 011 663 2097/011 650 7422