በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የልማትና ክርሰቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን በጦርነት ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸውና ቤታቸው ለፈረሰባቸው ማህበረሰቦች ለሚያከናውነው የሰብአዊ እርዳታ ስራዎች ለቤት መስሪያ የሚውል 32ጌጅ ወይም 35ጌጅ የሆኑ 2000 የጣራ ቆርቆሮ (Well Galvanized CIS Corrugated Iron Sheet) በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Ethiopian-Tewahido-Church-logo-Reportertenders-2

Overview

 • Category : Purchases
 • Posted Date : 02/19/2022
 • Phone Number : 0943076689
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 03/04/2022

Description

የግ» ጨረታ ማስታወቂያ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የልማትና ክርሰቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን በጦርነት ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸውና ቤታቸው ለፈረሰባቸው ማህበረሰቦች ለሚያከናውነው የሰብአዊ እርዳታ ስራዎች ለቤት መስሪያ የሚውል 32ጌጅ ወይም 35ጌጅ የሆኑ 2000 የጣራ ቆርቆሮ (Well Galvanized CIS Corrugated Iron Sheet) በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡-

ስነሆነም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ ድርጅቶች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

 • በጣራ ቆርቆሮ ምርት የደረጃ መዳቢዎች የብቃት ማረጋገጫ ሰርቲፊኬት ያለውና በቆርቆሮ ላይ የብቃት ማረጋገጫ ማህተም ያረፈበትን ማቅረብ የሚችል፣
 • በመስኩ የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ ያለው፣
 • የግብር ከፋይነት የምስክር ወረቀት ያለው፣
 • የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ምዝገባ መታወቂያ ያለው፣
 • የጨረታ ማስያዣ አራት ፐርስንት (4%) ሲፒኦ ማቅረብ አለበት፣
 • ኮሚሽኑ ጨረታውን ከከፈተ እና በዋጋና በዶክመንት ካወዳደረ በኃላ አሸናፊ የሆነው ድርጅት የሚያቀርበውን ቆርቆሮ በባለሙያ በማስገምገም ውሳኔ የሚሰጥበት ይኖሆናል፣

ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች፣ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ድረስ የመሸጫ ዋጋውን ከላይ በመስፈርቱ ላይ ከተዘረዘሩ ማስረጃዎች ጋር በሰም በታሸገ ኤንቮሎፕ ውስጥ በማድረግ በኮሚሽኑ ዋና መ/ቤት 1ኛ ፎቅ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፣

 • ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ኛው ቀን ከቀኑ በ8፡00 ስዓት ጨረታው ይዘጋል፡፡ በዚሁ ዕለት ከቀኑ በ8፡30 ጨረታው ስለሚከፈት በሰዓቱ ተጨራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው መገኘት ይችላሉ፣
 • ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣

አድራሻ

በኢ/ኦ/ተ/ቤተክርሰቲያን የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን

አራት ኪሎ ቱሪስት ሆቴል ፊት ለፊት

አዲስ አበባ

ለተጨማሪ ማብራሪያ ስ.ቁ 0943076689 ወይም 0911552683