ሉሲ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ ለሪከቨሪ ያርድ መጋዘን፣ የዋና መ/ቤት ቢሮ፣ እና የመኪና ማቆሚያ ግቢ/Parking/ቢሮዎችን ለማስጠበቅ የጥበቃ አገልግሎት ግዥ፣ እንዲሁም ለዋናው መ/ቤት ቢሮዎች እና ለተወሰኑ የአዲስ አበባ ቅርንጫፎች የጽዳት እና የመላላክ (ጽዳትና ተላላኪ) ስራዎችን ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

Lucy-insurance-logo

Overview

 • Category : Cleaning & Janitorial Service
 • Posted Date : 02/19/2022
 • Phone Number : 0114703361
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 03/04/2022

Description

  ጨረታ ቁጥር 001/2014

የጨረታ ማስታወቂያ

ሉሲ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ ለሪከቨሪ ያርድ መጋዘን፣ የዋና መ/ቤት ቢሮ፣ እና የመኪና ማቆሚያ ግቢ/Parking/ቢሮዎችን ለማስጠበቅ የጥበቃ አገልግሎት ግዥ፣ እንዲሁም ለዋናው መ/ቤት ቢሮዎች እና ለተወሰኑ የአዲስ አበባ ቅርንጫፎች የጽዳት እና የመላላክ (ጽዳትና ተላላኪ) ስራዎችን ለማሰራት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መመዘኛዎች ከሚያሟሉ ድርጅቶች አገልግሎቱን በኮንትራት ለማግኘት ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሰረት፡-

 1. የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ፤
 2. ከፌዴራል ፖሊስ የግል የጥበቃ ተቋማት ብቃት ማረጋገጫ ወረቀት ማቅረብ የሚችል እና ከሚመለከተው ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ስራና ሠራተኛ የማገናኘት አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ፈቃድ ያለው፣
 3. የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የስራ ልምዱን የሚገልጽ የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል፣
 4. ለንብረቱ የመድን ዋስትና (ለሪከቨሪ ያርድ መጋዘን እና ለመኪና ማቆሚያ ግቢ) ማቅረብ የሚችል፣
 • አገልግሎቱን ለማቅረብ ፍላጎቱ ያላቸው ድርጅቶች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር(10)   ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ቅዳሜን እስከ 6፡00 ሰዓት ድረስ የስራ ቦታዎቹን መመልከት ይችላሉ፡፡
 • ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቬሎፕ እስከ የካቲት 25 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በማግስቱ (የካቲት 26 ቀን 2014 ዓ.ም) ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
 • ኩባንያው ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ ለመሰረዝ ሙሉ መብት አለው፡፡

አድራሻ

22 ማዞሪያ ካፒታል ሆቴል ፊት ለፊት ዋሪት ሙሉ ጥላ አጠገብ ሉሲ ኢንሹራንስ አ.ማ ዋና መ/ቤት 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 301 ሰው ሀብትና ሎጅስቲክስ ቢሮ

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-470-33-61/011-470-58-77 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

ሉሲ ኢንሹራንስ አ.ማ