የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት በመንግስት የልማት ድርጅትነት የተመዘገበ የልማት ተቋም ሲሆን የውጭ ኦዲተሮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ የድርጅቱን የ2011 ዓ.ም. የሂሣብ እንቅስቃሴ ማስመርመር ይፈልጋል፡፡

Defence-Construction-Enterprise-11

Overview

 • Category : Auditing Related
 • Posted Date : 02/23/2022
 • Phone Number : 0118960626
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 03/09/2022

Description

ለውጭ ኦዲተር በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የማስታወቂያ ቁጥር DCDE/0011/2014

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት በመንግስት የልማት ድርጅትነት የተመዘገበ የልማት ተቋም ሲሆን የውጭ ኦዲተሮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ የድርጅቱን የ2011 ዓ.ም. የሂሣብ እንቅስቃሴ ማስመርመር ይፈልጋል፡፡ ተጫራቾችም የሚከተሉትን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡

 1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩ፣ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ “Tin” ሰርተፊኬት እና ተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ መሆን አለባቸው፡፡
 2. የዘመኑ ታክስ ለመከፈላቸው ከሚመለከተው አካል የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ አለባቸው፡፡
 3. በኦዲት ሥራ ላይ ለማሣተፍ የሚያስችላቸውን የሙያ ፈቃድ ወይም ሰርተፊኬት ከፌዴራል ኦዲት መምሪያ ወይም ከሚመለከተው ፈቃጅ አካል ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
 4. ተጫራቾች ለሌሎች ተቋማት የሰሩበት የተረጋገጠ የልምድ ማስረጃ የሚያቀርቡ መሆን አለባቸው፡፡
 5. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያቸውን ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ድርጅቱ በሚገኝበት አድራሻ በዋናው መ/ቤት ወሎ ሰፈር አምባሰል ህንፃ ፊት ለፊት ወይም ብራና ማተማያ ድርጅት ገባ ብሎ በአካል በመቅረብ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከግዥ ክፍል ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
 6. ተጫራቾች በመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት (Defence Construction Design Enterprise) ስም የተዘጋጀ ብር 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር) በCPO ማስያዝ አለባቸው፡፡
 7. ተጫራቾች ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ከ16/06/2014 ዓ.ም. ቀን እስከ 30/06/2014 ዓ.ም. ድረስ በተገቢው በማሸግ የጨረታ ሰነዳቸውን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በ30/06/2014 ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ጨረታው ተዘግቶ፤ 8፡30 ጨረታው ይከፈታል፡፡
 8. ሌሎች ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ ነው፡፡
 9. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡- የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት

ወሎ ሰፈር አካባቢ አምባሰል ህንፃ ፊት ለፊት ወይም ብራና ማተሚያ ድርጅት ዝቅ ብሎ

ስልክ ቁጥር 0118960626/29/32