ኖህ ትራንስፖርት አ.ማ ያገለገሉ ስካንያዎች፣ ኤሮትራከር፣ ከባድ የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪዎችን፤ ቮልቮ የህዝብ ማመላለሻ ትራንስፖርት አውቶቡስ 65 ወንበር ያለው፤ ሃይወንዳይ 12 ሰው የሚይዝ፣ ጃንቢ ሞዴል ሚኒባስ፣ ደብል ፒክአፕ ሞዴል ማዝዳ መኪናዎችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

NOAH-TRANSPORT-SHARE-COMPANY-logo

Overview

 • Category : Vehicle Sale
 • Posted Date : 02/23/2022
 • Phone Number : 0114402608
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 03/08/2022

Description

ያገለገለ ስካኒያ ኤሮትራከር የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ እና የትናንሽ መኪናዎች

ሽያጭ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

ኖህ ትራንስፖርት አ.ማ ያገለገሉ ስካንያዎች፣ ኤሮትራከር፣ ከባድ የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪዎችን፤ ቮልቮ የህዝብ ማመላለሻ ትራንስፖርት አውቶቡስ 65 ወንበር ያለው፤ ሃይወንዳይ 12 ሰው የሚይዝ፣ ጃንቢ ሞዴል ሚኒባስ፣ ደብል ፒክአፕ ሞዴል ማዝዳ መኪናዎችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም፡-

 1. ማንኛውም በጨረታው መካፈል የሚፈልግ ድርጅትም ሆነ ግለሰብ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 1ዐ ተከታታይ ቀናቶች ውስጥ ተሽከርካሪዎችን አዲስ አበባ ሳሪስ፣ ከሳሪስ ገበያ ማዕከል አቅራቢያ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና ቅጥር ግቢ በግንባር ቀርቦ ማየት ይችላል፡፡
 2. ተጫራቾች የተሽከርካሪዎችን ዝርዝር፣ ዓይነትና መጠን፣ የጨረታ መነሻ ዋጋ፣ ዝርዝር የሽያጭ መረጃና መስፈርት የያዘ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 1ዐዐ /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከድርጅቱ ፋይናንስ ክፍል ቢሮ ቁጥር 7 የጨረታውን ሰነድ መወሰድ ይችላሉ፡፡
 3. በጨረታው የሚሳተፉ ተጫራቾች ህጋዊ ሰውነት የተሰጣቸው ድርጅቶች ከሆኑ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የታደሰ የዘመኑ ንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዘገባ የምስክር ወረቀት የዘመኑ ግብር የከፈሉበትን ሰነዶች ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚገባቸው ሲሆን ግለሰቦች ከሆኑ ማንነታቸውን የሚገልጽ የነዋሪነት መታወቂያ፣ የመንጃ ፈቃድ ወይም ፓስፖርት ኮፒ አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
 4. ማንኛውም ተጫራች ለሚጫረተው ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪ የሚወዳደርበትን ዋጋ በተዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ሞልቶ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡
 5. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 2ዐ በመቶኛው በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ የ45 ቀናት ከጨረታው ሰነድ ጋር ማስገባት አለባቸው፡፡
 6. ተጫራቾች ተሽከርካሪዎቹን በመሉ ወይም በከፊል ለመግዛት ዋጋ ማቅረብ ይችላሉ፡፡
 7. የጨረታ ሰነድ መመለሻው በማብቃያው ቀን ሆኖ እስከ ቀኑ 6፡ዐዐ ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ሲሆን ጨረታው በዚሁ እለት ከቀኑ 7፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
 8. ተጫራች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ፊት ለፊት ላይ የተጫራቹ ሙሉ ስም፣ አድራሻ፣ ስልክ ቁጥር፣ እና ፊርማ ወይም ክብ ማህተም በግልጽ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል፡፡
 9. የጨረታውን ሰነድ ድርጅቱ ባዘጋጀው የጫረታ ሳጥን ውስጥ ቢሮ ቁጥር 4 በመገኘት ማስገባት አለባቸው፡፡
 10. ተጫራች ማሸነፉ በተገለፀለት በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በአክሲዮን ማህበሩ ሳሪስ አዋሽ ባንክ ቅርንጫፍ ተንቀሳቃሽ የሂሳብ ቁጥር C/A 01304103975400 ውስጥ ገቢ ማድረግ ግዴታ አለበት፡፡ ይህን ያላደረገ ተጫራች ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ በቅጣት መልክ ለአክሲዮን ማህበሩ ገቢ ሆኖ አሸናፊነቱ ይሰረዛል፡፡
 11. የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈውን ተሽከርካሪ መሉ ክፍያውን ከፈፀመበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናቶች ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለበት፡፡ በተቀመጠው የማንሻ የጊዜ ገደብ ወስጥ ተሽከርካሪውን ያላነሳ የጨረታ አሸናፊ ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪ በቀን ብር 1ዐዐ (አንድ መቶ ብር)  የማቆያ ኪራይ ክፍያ የመክፈል ግዴታ አለበት፡፡
 12. ለጨረታ የቀረቡት ተሸከርካሪዎች የሚፈለግባቸውን ማንኛውንም ውዝፍ እዳና የስም ማዘዋወሪያ ክፍያ የጨራታው አሸናፊ የመክፈል ግዴታ አለበት፡፡
 13. አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈውን ተሽከርካሪ /መኪና ከድርጅቱ ግቢ በራሱ ትራንስፖርት አጓጉዞ ያነሳል፡፡
 14. ኖህ ትራንስፖርት አ.ማ በጨረታው የተሻለ አማራጮችን ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 አድራሻ፡- ኖህ ትራንስፖርት አክስዮን ማህበር ዋናው መስሪያ ቤት

ሣሪስ ከሪስ ኢንጅነሪንግ ወረድ ብሎ ከዩኒቨርሳል ቆዳ ፋብሪካ ፊት ለፊት

 ስልክ ቁጥር 0114 4026 08 / 0114 42 55 21/ 0911 20 77 07