የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ 10 ኪሎ ዋት ከፀሐይ ኃይል የኤሌክትክ ማመንጫ መሳሪያ (ሶላር ፓነል) ለመትከል እና የተተከለው ሶላር ፓነል መስራቱን በሙከራ አረጋግጦ፣ኮሚሽኒንግ ሰርቶ ለማስረከብ የሚችል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡

Ethiopian-Academy-of-Sciences-Eas-logo

Overview

  • Category : Solar & Photovoltaic
  • Posted Date : 02/23/2022
  • Phone Number : 0911695382
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 03/04/2022

Description

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ከፀሐይ ኃይል የኤሌክትክ ማመንጫ መሳሪያ  ተከላ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ 10 ኪሎ ዋት ከፀሐይ ኃይል የኤሌክትክ ማመንጫ መሳሪያ (ሶላር ፓነል) ለመትከል እና የተተከለው ሶላር ፓነል መስራቱን በሙከራ አረጋግጦ፣ኮሚሽኒንግ ሰርቶ ለማስረከብ የሚችል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚህም መሰረት በጨረታው ላይ መሳተፍ የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የሚያሟሉ ህጋዊ ሰውነት ያላቸው ድርጅቶች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በጨረታው በዘርፉ ህጋዊና የዘመኑን ግብር ከፍለው የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉበት የግብር ክሊራንስ መረጃ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የቲን ሰርተፊኬት እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰተርተፍኬት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ሁሉ መወዳደር ይችላሉ፡፡
  2. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ አስተዳደር ቢሮ ድረስ በመምጣት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው የቴክኒካልና የዋጋ መግለጫዎች አንድ ኦሪጅናልና ሁለት ኮፒዎችን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ማስታወቂያው በአማርኛ ሪፖርተር ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ማቅረብ ይችላሉ፡፡
  4. ጨረታው በ10ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4:30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአካዳሚው የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ በግልፅ ይከፈታል፡፡
  5. አካዳሚው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊልየመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልግ በስልክ ቁጥር 0911-695382 ወይም 0112570930 ደውለው ወይም በአካል መጠየቅ ይችላሉ፡፡

ከቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ወደ ዊንጌት በሚወስደው መንገድ ላይ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጉለሌ ቅርንጫፍ አልፎ በቀኝ በኩል በሚታጠፈው መንገድ 500 ሜትር ያህል ገባ ብሎ ከሚገኘው የአካዳሚው ዋና መ/ቤት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን እንዲገዙ እና እንዲወዳደሩ እንጋብዛለን፡፡