ሴንድ ኤ ካው ኢትዮጵያ ጥራታቸውን የጠበቁ እና የተሻሻሉ የፍራፍሬ ችግኞችን በዘርፉ ልምድና ተገቢው ህጋዊ ፈቃድ ካላቸው አቅራቢዎች ገዝቶ ማሰራጨት ይፈልጋል፡፡

Send-a-Cow-Reportertenders-2

Overview

  • Category : Flora & Horticulture
  • Posted Date : 02/27/2022
  • E-mail : Mesfin.Zenebe@sendacow.org
  • Phone Number : 0116477233
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 03/14/2022

Description

ፍራፍሬ ችግኝ ግዢ ጨረታ ማስታወቂያ

ሴንድ ኤ ካው ኢትዮጵያ በደቡብ ብሔር፡ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልላዊ መንግስት በወላይታ ዞን በሚገኙ 3 ወረዳዎች የሚገኙ አርሶ አደሮችን ገቢና ስርዓተ ምግብ ማሻሻል ላይ ያተኮረ ፕሮጀክት በመተግበር ላይ ይገኛል፡፡ በመሆኑም ድርጅቱ በፕሮጀክቱ የታቀፉ አርሶ አደሮች ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያግዙ ጥራታቸውን የጠበቁ እና የተሻሻሉ የፍራፍሬ ችግኞችን በዘርፉ ልምድና ተገቢው ህጋዊ ፈቃድ ካላቸው አቅራቢዎች ገዝቶ ማሰራጨት ይፈልጋል፡፡ሰለሆነም ድርጅታችን በዘርፉ የተሰማራችሁና ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ህጋዊ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩተን የፍራፍሬ ችግኝ ዓይነቶች ለማቅረብ እንድትወዳደሩ ይጋብዛል።

ተ/ቁ የፍራፍሬ ዓይነት መለኪያ በዛት ለዩ መግለጭ
1 የአቮካዶ ችግኝ ቁጥር 24,200 የተከተበ /Grafted/ ሃስ ዝርያ /Hass/ እና ኤቲንገር /Ettinger/
2 የማንጎ ችግኝ ቁጥር 11,000 የተከተበ /Grafted/ ኬንት /Kent/፣ አፕል ማንጎ /Apple mango/ ወይም ቶሚ ሃትኪንስ /Tommy Atkins/
3 የአፕል ችግኝ ቁጥር 8,800 የተከተበ/Grafted/ ክሪስፒን /Crispin/ አና /Anna/ ጎልደን ዴሊሺየስ /Golden delicious/ ዝርያዎች

በዘርፉ የተሰማራችሁ ህጋዊና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላችሁ ተጫራቾች የዚህ ግልጽ ጨረታ ዝርዝር ሂደት የያዘውን የጨረታ ሰነድ ከዚህ በታች በተጠቀሰው መንገድ በመውሰድ የጨረታ ሰነዶቻችሁን በታሸገና የድርጅቱ ማህተም ባረፈበት ፓስት አደርጎ በማስገባት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

የጨረታ ሰንድ ማስገቢያው ይህ ግልጽ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት የመጀመሪያው የስራ ቀን አንስቶ ባሉት 10 /አስር/ የስራ ቀናት ሲሆን መጋቢት 5 ቀን 2014 ዓም ከቀኑ 10 ስዓት ላይ የሚዘጋ ይሆናል፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለ2014 ዓም የታደሰ የንግድ ፈቃድና የንግድ ምዘገባ ሰርተፊኬት ድጅታል ቅጂ በ Mesfin.Zenebe@sendacow.org ወይም Aster.Abreha@sendacow.org በመላክ በኢሚይል አድርሻችሁ ማግኘት የምትችሉ ሲሆን በተጨማሪም ከታች ከተገለጹት የድርጅቱ አድራሻዎች በአካል በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

የጨረታ ሰነድ መውሰጃና የጨረታ ዶክመንት ማስገቢያ አድራሻ

  1. ሴንድ ኤ ካው ኢትዮጵያ አዲስ አበባ ከመገናኛ ወደ ሲምሲ መንገድ ሲቪል ሰርቪስ አለፍ ብሎ ከጊብሰን ት/ቤት ፊት ለፊት ጎልጎታ ህንጻ 7ተኛ ፎቅ     ስልክ ቁጥር 011-647-72-33/34/35/09 11 70 41 65
  1. ሴንድ ኤ ካው ኢትዮጵያ ወላይታ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ወላይታ ሶዶ ስልክ፡ 046 180 40 11

ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡