ሁንዴ ኦሮሞ ግራስሩትስ ደቨሎፕመንት ኢኒሼቲቭ በጅማ ዞን በመና ወረዳ ለሚገኙ ማህበረሰብ ውሃ ፓምፕ ማድረጊያ ሶላር አወዳድሮ በመግዛት ማስተከል ይፈልጋል፡፡

Overview

  • Category : Solar & Photovoltaic
  • Posted Date : 02/27/2022
  • Phone Number : 0115584623
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 03/17/2022

Description

የጨረታ ማስታወቅያ

ድርጅታችን ሁንዴ ኦሮሞ ግራስሩትስ ደቨሎፕመንት ኢኒሼቲቭ በጅማ ዞን በመና ወረዳ ለሚገኙ ማህበረሰብ ውሃ ፓምፕ ማድረጊያ ሶላር አወዳድሮ በመግዛት ማስተከል ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም የታደሰና ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፤ ህጋዊ የሆነ ደረሰኝ ማቅረብ የሚችሉና በጨረታ ሰነዱ ላይ የተዘረዘሩ መስፋርቶችን የሚያሟሉ ድርጅቶች የጨረታ ሰነዱን 200 ብር በመክፈል ከድርጅቱ መግዛት የሚችሉ ሲሆን የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ የሚጫረቱበት ጠቅላላ ዋጋ 2/በመቶ በሁንዴ ኦሮሞ ግራስሩትስ ደቨሎፕመንት ኢኒሼቲቭ ስም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ/ሲፒኦ/ ከጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ጋር በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንሰቶ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በአዲስ አበባ መስቀል ፍላዎር አደባባይ አከባቢ በሚገኘው ቪላ ቨርዴ ሆቴል አጠገብ ባለው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ማቅረብ ይችላሉ፡፡

የጨረታ መወዳደሪያ ሰነዱን ማስገባት የሚቻለው በአሥራ አምስቱም ተከታታይ ቀናት ሲሆን በአሥራ አምስተኛው ቀን ግን እስከ ረፋዱ 5፡00 ሰዓት ብቻ ይሆናል፡፡ ጨረታው በዚያው ቀን ከረፋዱ በ5፡01 ተዘግቶ በዚያው ቀን ከረፋዱ በ5፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፡፡ አሥራ አምስተኛው ቀን የሥራ ቀን ላይ የማይውል ከሆነ ጨረታው ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ላይ ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡

ጨረታውን የሚያሸንፍ ድርጅት ሶላሩን በቦታው ድረስ በማጓጓዝ፣ የተከላ ሥራውን በማከናወን፣ እንደዚሁም ለአገልግሎት ዝግጁ በማድረግ ማስረከብ ይኖርበታል፡፡ ተጫራቾች የሶላሩን ዝርዝር መግለጫ (Specification) ከድርጅቱ ማገኘት ይችላሉ፡፡

S/N  Item Description Unit Quantity
1 Monocrystalline PV generator system (Solar module) to supply the required power, including the required size of cable. The PV to be installed is 150 meters away from the pump house. Ls 1
2 Control unit (RSI) for monitoring, protecting, and controlling pump operation including all accessories and housing for the control equipment etc. Ls 1
3 Class-B, 2 1/2″ Galvanized steel structure for ground mounting (panel support with aluminium module clamps) with 40X40 L-section horizontal painted mild steel beam with all requried bolts, nuts and washer and having all required other accessories. The height above the ground should not be less than 1m. Ls 1
4 Transportation, Installation and commissioning     Ls 1

ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ በስ.ቁ 011 558-46-23/011558-2328 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡