መልካ አዋሽ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ዩኒዬን ለ2014/15 የምርት ዘመን የሚውል የአፈር ማዳበሪያዎችን ከሰበታ ከተማ ዳላቲ 06 ቀበሌ ሰበታ ወረዳ ፤ ቀርሳ ማሊማ እና ሶዶ ዳጪ ወረዳዎች በዩኒዬኑ ሥራ ክልል ስር ላሉት መሰረታዊ የገበሬዎች ህብርት ሥራ ማህበራት ማጓጓዝ ይፈልጋል፡፡

Melca-Ethiopia-logo-1

Overview

 • Category : Transport Service
 • Posted Date : 02/26/2022
 • Phone Number : 0912048744
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 03/14/2022

Description

የአፈር ማዳበሪያ ማጓጓዥያ ጨረታ

መልካ አዋሽ  የገበሬዎች ህብረት ሥራ ዩኒዬን ለ2014/15 የምርት ዘመን የሚውል የአፈር ማዳበሪያዎችን  ከሰበታ  ከተማ ዳላቲ 06 ቀበሌ  ሰበታ ወረዳ ፤ ቀርሳ ማሊማ እና ሶዶ ዳጪ ወረዳዎች  በዩኒዬኑ ሥራ  ክልል ስር ላሉት መሰረታዊ የገበሬዎች ህብርት ሥራ ማህበራት ማጓጓዝ ይፈልጋል፡፡ስለዚህ  በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ሕጋዊ የደረቅ ጭነት ማመላለሻ ባለንብረቶች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፤

ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው ግዴታዎች፡

 1. የ2013 ወይም 2014 ዓ.ም የታደሰ ሥራ ፊቃድ ማቅረብ የሚችል፤
 2. የጨረታ ሰነዳቸውን ሞልተው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ከጠዋቱ 4፡00  ሰዓት ድረስ ያስገባሉ፡፡
 3. የማጓጓዣ ታሪፍን በተመለከተ አንዱን ኩንታል ከሚጫንበት መጋዘን እስከ መሠረታዊ የህብረት ሥራ ማህበራት የሚያጓጉዙበትን ድረስ ዋጋ ኩንታል በኪሎሜትር(price in quital per kilometre) መስጠት አለባቸው፤
 4. ተጫራቾች ያላቸውን የመኪናዎች ብዛት እና የመጫን ችሎታ በተመለከተ ከሚመለከተው የመንግሥት አካል ለዘመኑ የታደሰ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
 5. ተጫራቾች ለጨረታው በሚቀርቡበት ወቅት ቢያንስ የሁለት ዓመት የቅርብ ጊዜ (የ2012 እና የ2013 ዓ.ም) የማጓጓ´ የስራ ልምድ እና መልካም የስራ አፈጻጸም ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው፡፡
 6. ከተወዳዳሩበት የአፈር ማዳበሪያ ብዛት ጋር የሚመጣጠን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 5% CPO ማስያዝ አለበት፡፡
 7. የጨረታው ማስከበረያ ለተሸናፊዎች ሲመለስላቸው አሸናፊዎች ግን ሥራውን በተዋዋሉት መሠረት ሲያጠናቅቁ የሚመለስላቸው ይሆናል፡፡
 8. ተጫራቾች /ተወካዮቻቸው/ በጨረታው መክፈቻ ላይ ለመገኘት ከድርጅቱ የውክልና ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ለተወዳዳሪዎች በሙሉ ባይገኙም በተገኙት ፊት ጨረታው ይከፈታል፡፡
 9. የማራገፈያ ጣቢያዎቹን እና የማዳበሪያውን ብዛት የሚገልጽ ሰነድ ከዩኒዬኑ ቢሮ ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሥራ ሰዓት የማይመለስ 1,000.00 (አንድ ሺህ ) ብር በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
 10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ቀን ከቀኑ በ4፡00 ታሽጎ በ4፡30 ሰዓት ጧት በዩኒዬኑ ቢሮ ይከፈታል፡፡ 10ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
 11. አንድ ተጫራች በሌላው ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም፡፡
 12. በተቀራራቢ ጣቢያዎች ላይ የተጋነነ የዋጋ ልዩነቶችን ለማስታረቅ ሲባል ዩኒዬን የራሱን አማራጭ መውሰድ ይችላል፡፡
 13. ተጫራቾች ከተራ ቁጥር 1-8 ማሟላት ያለባቸው ግዴታዎች ኦርጅናል እና ፎቶ ኮፒ በመለየት በሰም በታሸገ ፖስታ የድርጅቱ ማህተም እና ስም ተደርጎበት መቅረብ አለበት፡፡
 14. ዩኒዬኑ በትራንስፖርት ጨረታው ላይ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፤- መልካ አዋሽ  የገ/ህ/ሥራ ዩኒዬን : ሰበታ ከተማ የሰበታ ሀዋስ ወረዳ  ግብርና ቢሮ በሚገኛው ጊቢ የመልካ አዋሽ  የገ/ህ/ሥራ ዩኒዬንጽ/ቤት ፤ለበለጠ መረጃ በ ስልክ ቁጥር  0912048744 / 0913101921