ሰላም የህዝብ ማመላለሻ አ.ማ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት መለዋወጫ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛትና መሸጥ ይፈልጋል፡፡

Overview

 • Category : Spare Parts Sale & Supply
 • Posted Date : 02/28/2022
 • Phone Number : 0914706518
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 03/21/2022

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ሰላም የህዝብ ማመላለሻ አ.ማ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት መለዋወጫ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛትና መሸጥ ይፈልጋል፡፡

Dot 1. የአዉቶብሶቻችን መለዋወጫ ዕቃዎች፣ ጎማዎች፣ዘይትና እና ቅባቶች ለመግዛት

Dot 2.. የሰራተኞች ደንብ ልብስ  ጫማዎችና ሸሚዝ የመሳሰሉት ለመግዛት

Dot 3. የስካንያና የዩቶንግ አዳዲስ መለዋወጫ ዕቃዎች መሸጥ ይፈልጋል

Dot 4.ያገለገሉ ጎማዎች መለዋወጫ ዕቃዎች የተቃጠሉ ዘይቶች እንዲሁም ብረታ ብረቶች የመሳሰሉት መሸጥ ይፈልጋል ፡፡

ስለዚህ ፡-

 1. ተጫራቶች በየዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ የአቅራቢነት የምዝገባ የምስክር ወረቀት፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት እና TIN ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸዉ፡፡
 2. የጨረታ ማስከበርያ በአጠቃላይ የሚያቀርቡትን ዋጋ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲፒኦ ማቅረብ የሚችል መጠኑ በሚገዙት ሰነድ የሚገለፅ ይሆናል፡፡
 3. በየዘርፉ የተዘጋጁትን የጨረታ ሰነዶች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 07(ሰባት) ተከታታይ ቀናት ድረስ የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) በመክፈል ሰነዱን ቢሮ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
 4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ቢሮ በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
 5. ጨረታዉ የካቲት 30/2014 ዓ/ም ከሰኣት በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በ8፡30 በድርጅቱ መሰብሰብያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
 6. ለአሸናፊ ድርጅት ወይም ድርጅቶች አሸናፊነታቸው በተገለፀዉ በአስር ቀናት ዉስጥ ዕቃውን ማስገባት ይኖርባቸዋል፣ አሸናፊ ድርጅቶች አሸናፊነታቸዉ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ለ15 ቀናት የዕቃዎቹ ዋጋ ፀንቶ የሚቆይ ይሆናል፡፡
 7. አሸናፊ ድርጅት ወይም ድርጅቶች አሸናፊነታቸው በተገለፀ በአንድ ሳምንት ዉስጥ ዕቃውን ማንሳት ይኖርባቸዋል፣ ይህ ሳያደርጉ ቢቀሩ ግን ያስያዙት የጨረታ ማስከበርያ ገንዘብ (ሲፒኦ) ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ እቃው በድጋሚ በጨረታ ይወጣል፡፡
 8. ተጫራቶች ያንዱን ዋጋ ከነቫቱ በመሙላት ማሳወቅ ይጠበቅባቸዋል፡፡ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡

 ሰላም የሕዝብ ማመላለሻ አክስዮን ማህበር

ዮሴፍ ቤተክርስትያን ፊት ለፊት

አዲስ አበባ

   ለተጨማሪ ማብራሪያ   በስልክ ቁጥር 0914706518/0912994892 ደውለዉ ይጠይቁ