ሚድሮክ ኮንስትራክሽን ኢትዮጵያ ኃላ/የተ/የግል ኩባንያ ከታች የተገለጹትን ተሸከርካሪዎችና ማሽነሪዎች ባሉበት ሁኔታ (ይዞታ) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

MIDROC-Construction-Ethiopia-PLC-logo

Overview

 • Category : Purchases
 • Posted Date : 03/02/2022
 • Phone Number : 0113718902
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 03/18/2022

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ሚድሮክ ኮንስትራክሽን ኢትዮጵያ ኃላ/የተ/የግል ኩባንያ ከታች የተገለጹትን ተሸከርካሪዎችና ማሽነሪዎች ባሉበት ሁኔታ (ይዞታ) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

ተ.ቁ. የዕቃው ዓይነት ብዛት መለኪያ ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ የጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት በተናጥል የጨረታ ማስከበሪያ መጠን
1. Loader 7  

 

 

 

 

 

 

 

በቁጥር

 

 

 

 

 

 

 

 

60 ቀን

 

 

 

 

 

 

 

መጋቢት 20 ቀን 2014 ዓ.ም. ከሰዓት 8፡00

 

 

 

 

 

 

 

መጋቢት 20 ቀን 2014 ዓ.ም. ከሰዓት 8፡30

 

 

 

 

 

 

 

100,000 ብር

2 Micro Bus 4
3 Dump Truck 6
4 Automobile 6
5 Tractor Truck 1
6 Station Wagon 2
7 Bus 1
8 Motor Cycle 1
9 Pick-up double cabin 3
10 Concrete mixer 3
11 Concrete Pump 1
12 Chevrolet Van 2
13 Tower Crane 2
14 Compactor 7
15 Generator 3
16 Excavator 3
17 Walk Behind 1
18 Grader 1
19 Dumper 1
20 Crusher 1
21 HCB Machine with Mold 1
22 Asphalt Heater 1
23 Air Compress 1
24 Mobile Crain 1
25 Jack Hammer 2

ስለዚህ

 1. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ከየካቲት 28 ቀን 2014 ዓ.ም. እስከ መጋቢት 20 ቀን 2014 ዓ.ም. ድረስ መቻሬ ሜዳ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መሥሪያ ቤት ፕሮኪዩርመንትና ሎጀስቲክስ ክፍል መግዛት ይችላሉ፡፡
 2. ድርጅቱ ለጨረታ ያቀረባቸውን ተሸከርካሪዎች ተጫራቾች ከየካቲት 28 ቀን 2014 ዓ.ም. እስከ መጋቢት 19 ቀን 2014 ዓ.ም. ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት (ጠዋት 3፡00-6፡00 እንዲሁም ከምሳ በኋላ ከ7፡30 እስከ 10፡00 ድረስ) በአካል በመቅረብ ማየት ይችላሉ፡፡ ለማየት ሲመጡ ሰነድና ሕጋዊ መታወቂያ መያዝ የሚያስፈልግ ሲሆን መኪና ይዞ መግባት ግን በፍጹም አይፈቀድም፡፡
 3. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ተሸከርካሪ የጨረታ ማስረከቢያ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) 100,000 ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
 4. ማንኛውም ተጫራች የመጫረቻ ሰነዱን በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ መጋቢት 20 ቀን 2014 ዓ.ም. ከ2፡00 – 8፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ በድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
 5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት መጋቢት 20 ቀን 2014 ዓ.ም. ከምሳ በኋላ 8፡30 ሰዓት ላይ በድርጅቱ ዋና መ/ቤት አዳራሽ ይከፈታል፡፡
 6. የተሻለ (ከፍተኛ) ዋጋ ያቀረበ የጨረታው አሸናፊ ሲሆን አንድ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ግን በፍጹም አይቻልም፡፡
 7. በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ለአሸናፊው ግለሰብ/ድርጅት በደብዳቤ ከተገለፀ በኋላ ሲመለስላቸው ለአሸናፊው ግን ከግዢው ክፍያ ጋር ታሳቢ ይሆናል፡፡
 8. የጨረታ አሸናፊው ከሚገዛቸው ተሸከርካሪዎች ጋር የተያያዙ ማንኛውንም (ሁሉንም) ክፍያዎች (እንደ የባለቤትነት ማረጋገጫ የስም ማዞር ክፍያ፣ የተጠራቀመ ዓመታዊ የቦሎ ክፍያና የመሳሰሉትን) መሸፈን ይጠበቅበታል፡፡ በተጨማሪም ላሸነፈበት ተሸከርካሪ የመጫኛ፣ የማጓጓዣ የክሬንና ፎርክሊፍት ወጪዎችንም የሚሸፍን ይሆናል፡፡
 9. የጨረታ አሸናፊው ያሸነፈበትን ዋጋ ከፍሎ በ15 ቀን ጊዜ ውስጥ ንብረቶቹን ማንሳት ይኖርበታል፡፡ ይህ ሳይሆን ቢቀር ግን ያስያዘው ገንዘብ (ሲፒኦ) ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ የጨረታ አሸናፊነቱ ይሰረዛል፡፡
 • ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ማሳሰቢያለበለጠ ማብራሪያ 0113 71 89 00 /0113 72 61 50/ 0113 71 89 05

አድራሻ፡- ሚድሮክ ኮንስትራክሽን ኢትዮጵያ ኃላ/የተ/የግል ኩባንያ  (መቻሬ ሜዳ ግቢ ውስጥ እንገኛለን)