የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለአምቦ ወሊሶ የመንገድ ሥራ ፕሮጀክት፣ ሀሮ ወንጪ ኢኮቱሪዝም የመንገድ ሥራ ፕሮጀክት፤ ሆምቾ አሙኔሽን ኢንጂነሪንግ ፕሮጀክት ግንባታ አገልግሎት የሚውሉ 60/70 እና 80/100 የሆነ የአስፓልት ቢትመን ግዥ ለመፈፀም በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
Overview
- Category : Construction Service & Maintenance
- Posted Date : 03/02/2022
- E-mail : INFO@dce-et.com
- Phone Number : 0114403434
- Source : Reporter
- Closing Date : 03/21/2022
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡-DCE/BM/22/2022
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለአምቦ ወሊሶ የመንገድ ሥራ ፕሮጀክት፣ ሀሮ ወንጪ ኢኮቱሪዝም የመንገድ ሥራ ፕሮጀክት፤ ሆምቾ አሙኔሽን ኢንጂነሪንግ ፕሮጀክት ግንባታ አገልግሎት የሚውሉ 60/70 እና 80/100 የሆነ የአስፓልት ቢትመን ግዥ ለመፈፀም በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም፡-
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩ፤ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ እና በጨረታ ለመወዳደር የሚያስችላቸው ከግብር ሰብሳቢው ባለስልጣን የተሰጠ የታደሰ ታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚያቀርቡት ገንዘብ በተጫራቾች መመሪያ አንቀፅ 4 ተራ ቁጥር 4.2 “b” በተጠቀሰው መሠረት መሆን አለበት፡፡
- አንድ ተጫራች መወዳደር የሚችለው በአንድ ዓይነት ምርት (ብራንድ) ብቻ ነው፡፡ በአማራጭ የቀረበ ዋጋ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ወሎ ሠፈር አካባቢ በሚገኘው የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ዋናው መ/ቤት የግንባታ ግብዓት እና ምህንድስና ግዥ ቡድን ቢሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ መጋቢት 13/2014 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው መጋቢት 13/2014 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡15 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡– የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ
የቀጥታ ስልክ ቁጥር 0114-40-34-34
ማዞሪያ 0114-42-22-70/71/72
ፖሳ.ቁ 3414 ፋክስ ቁ. 0114-40-04-71/0114-42-07-46
ወሎ ሰፈር የቀድሞው ኖሬላ ግቢ
ድህረ ገፅ፡- www.dce.et.com
ኢሜል፡-INFO@dce-et.com