የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ከዚህ በታች የዘረዘሩትን (የተጠቀሱትን) የማሽነሪ እና ጀኔሬተር – መለዋወጫዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
Overview
- Category : Other Sale
- Posted Date : 03/02/2022
- E-mail : INFO@dce-et.com
- Phone Number : 0114403434
- Source : Reporter
- Closing Date : 03/23/2022
Description
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የማሽነሪ እና ጀኔሬተር መለዋወጫዎችን ለመሸጥ የተዘጋጀ የሽያጭ ጨረታ ቁጥር ንብ/008/2014 ማስታወቂያ
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ከዚህ በታች የዘረዘሩትን (የተጠቀሱትን) የማሽነሪ እና ጀኔሬተር – መለዋወጫዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
- የካት መለዋወጫ ………………………………………………………………………………. ብዛት በቁጥር 6,507
- የኮማትሱ መለዋወጫ ……………………………………………………………………….. ብዛት በቁጥር 488
- የደሬስታ መለዋወጫ ………………………………………………………………………… ብዛት በቁጥር 2,950
- የጀኔሬተር መለዋወጫ …………………………………………………………………….. ብዛት በቁጥር 524
ድምር ……………………………………………………………………………… 10,469
በሽያጭ ጨረታው ለመሳተፈ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ማሟላት አለባቸው፡፡
- በሸያጭ ጨረታው ላይ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት ሊወዳደር ይችላል፡፡
- የሽያጭ ጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) ለድርጅታችን ፋይናንስ የሥራ ሂደት ገቢ በማድረግ ከንብረት አስተዳደርና አቅርቦት የሥራ ሂደት ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች ለሽያጭ የተዘጋጁትን የማሽነሪና ጀኔሬተር መለዋወጫዎች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ባሉት የሥራ ቀናት ጠዋት ከ3፡00 እስከ 6፡30 ከሰዓት ከ7፡30 እስከ 10፡30 ሰዓት ቃሊቲ በሚገኘው የድርጅቱ ግቢ በአካል በመገኘት መመልከት ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የማሽነሪና ጀኔሬተር መለዋወጫዎቹን በተናጠል ወይም በጥቅል ለመግዛት መጫረት ይችላል፡፡
- የተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያን በተመለከተ፡-
- የተለያዩ የማሽነሪና ጀኔሬተር መለወወጫዎች የጨረታ ማስከበሪያ በጥቅል ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ) በድርጅታችን ትክክለኛ ስም “መከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ” በሚል አሰርተው CPOውን ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር በማያያዝ የጨረታ ሳጥኑ ውስጥ ጨረታው ከሚከፈትበት መጋቢት 13 ቀን 2014 ጠዋት 4፡00 ሰዓት በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው መጋቢት 13 ቀን 2014 ዓ.ም. ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ቀን በ4፡15 (አራት ሰዓት ከሩብ) ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ስልክ ቁጥር
011-4-40-34-34
ማዞሪያ 011-4-42-22-70/71/72
E-mail አድራሻ Info@dce-et.com
የደህረ ገጽ አድራሻ dce-et.com Info@dce-et.com
ፖ.ሳ.ቁ. 3414 114-40-04-71/0114-42-07-46
ወሎ ሰፈር የቀድሞው ኖሬላ ግቢ