የአፍሮገነት ጥምር አገልግሎት ህንጻ ግንባታ አክስዮን ማህበር የድርጅቱን የፋይናንስ እና አስተዳደር መመሪያ (ማኗል) ባለሙያዎች በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

Overview

  • Category : Financial Consultancy
  • Posted Date : 03/07/2022
  • Phone Number : 0118549510
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 03/25/2022

Description

አፍሮገነት የጥምር አገልግ ህንጻ ግንባታ አክስዮን ማህበር

የጨረታ ማስታወቂያ

የፋይናንስ እና አስተዳደር መመሪያ (ማኗል) ለማሰራት የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የአፍሮገነት ጥምር አገልግሎት ህንጻ ግንባታ አክስዮን ማህበር የድርጅቱን የፋይናንስ እና አስተዳደር መመሪያ (ማኗል) ባለሙያዎች በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በሙያው ብቃትና ልምድ ያላቸው ተጫራቾች መሳተፍ እንዲችሉ በዚህ ማስታወቂያ ተጋብዘዋል፡፡

በዚሁ መሰረት የሙያ ፈቃድ ያላቸው ሆኖ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያሳይ ሙሉ መረጃ በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ እስከ 15 ቀን ድረስ የመወዳደሪያ ዋጋቸውን እና ዝርዝር መረጃቸው (PROPOSAL) በመያዝ ሰንጋ ተራ ከድሮ ደሳለኝ ሆቴል ፊት ለፊት በሚገኘው የቦርድ ጽ/ቤት በአካል ቀርበው እንዲያስገቡ እናሳውቃለን፡፡

ድርጅቱ ስለጨረታው የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው አይገደድም፡፡

ከሰላምታ ጋር

ሚፍታህ ከድር

ዋና ስራ አስኪያጅ

 ለበለጠ መረጃ ስ.ቁ፡- 01 18 54 95 10 / 09 11 20 52 78 / 09 11 67 40 50