አቢሲንያ ባንክ /አ.ማ/ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዛቸውንና በሠንጠረዡ የተመለከቱትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 (እንደተሻሻለው) መሠረት ንብረቶቹ ባሉበትግብር ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
Overview
- Category : House & Building Foreclosure
- Posted Date : 03/05/2022
- Phone Number : 0115150711
- Source : Reporter
- Closing Date : 04/07/2022
Description
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
አቢሲንያ ባንክ /አ.ማ/ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዛቸውንና በሠንጠረዡ የተመለከቱትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 (እንደተሻሻለው) መሠረት ንብረቶቹ ባሉበትግብር ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋውን ¼ (አንድ አራተኛ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲ.ፒ.ኦ በአቢሲንያ ባንክ (አ.ማ) ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው ለመሳተፍ ይችላሉ፡፡
- የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ከፍሎ በጨረታ ያሸነፈበትን ንብረት/ንብረቶች መረከብ ይኖርበታል፡፡ በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፡፡ በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ይመለስላቸዋል፡፡
- ተበዳሪው/መያዣ ሰጪው በሐራጁ ቀንና ሰዓት በቦታው መገኘት ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ባይገኙ ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎችን ፣ግብር፤በተተቀሱት ንብረቶች ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ 15 % ቫት እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውም ወጪዎች ገዢ ይከፍላል፡፡ውዝፍ የሊዝ ዕዳ ባንኩ የሚከፍል ሲሆን ቀሪ የወደፊት የሊዝ ክፍያ ዕዳ ወደ አሸናፊው /ገዢ የሚተላለፍ ይሆናል፡፡
- ንብረቶቹን በሥራ ሰዓት ፕሮግራም አሲዞ ለመጎብኘት ወይም ለማየት ይቻላል፡፡
- በባንኩ ብድር ፖሊሲ እና መመሪያ መሠረት መስፈርቱን ለሚያሟሉ የጨረታው ከፍተኛ ዋጋ አቅራቢዎች ባንኩ ከፊል ብድር ሊሰጥ ይችላል፡፡
- የጨረታው ቦታ አ.አ ከተማ ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 4 የቀድሞው ህብረት ባንክ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት ጎን ካለው አልፓውሎ ህንጻ 3ኛ ፎቅ በባንኩ ህግ መምሪያ ጽ/ቤት ነው፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0115-150711 እና 0115 54 67 37/36 አ.አ በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
t.q$ |
የተበዳሪው ስም | ከተበዳሪው የሚፈለግበት
ቀሪ ዕዳ |
የመያዣው ሰጪው ስም | የንብረቱ ዓይነትና አገልግሎት | የቦታው ስፋት | የባለቤት ማረጋገጫ ካርታ ቁጥር | ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ | የጨረታ መነሻ ዋጋ | ጨረታው የሚካሄድበት ቀን |
የምዝገባ ሰዓት |
የጨረታ
ሰዓት |
ጨረታው የወጣበት ጊዜ |
1 |
አቶ አበበ ወርቁ | እስከ ሐምሌ 19 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ብር4,610,812.51 | ገ ወ/ይ.ገነት ወ/አምላክ | መኖሪያ ቤት | 139.27ካ.ሜ | OR042041402010 | በኦ/ብ/ክ/መ ለገጣፎ lከተማ | 2,773,629.68 | መጋቢት28 ቀን 2014 ዓ.ም | 4:30-5:30 | 5:30-6:00 |
በድጋሚ |
2 |
አቶ ለማ ደበላ ቡልቡላ | እስከመስከረም
19 ቀን 2014ዓ.ም ድረስ ብር1,097,114,01 |
አቶ ለማ ደበላ | መኖሪያ ቤት | 337ካ.ሜ | BMD-/2008/G-02-195/”00” | በኦ/ብ/ክ/መ
ዱከም ቀበሌ ኮትቻ |
908,400.00 | መጋቢት29ቀን 2014 ዓ.ም | 4:30-5:30 | 5:30-6:00 |
ለመጀመሪያ |