የክርስቲያን በጎ አድራጎትና ልማት ማህበራት ህብረት የቢሮ ህንፃ የዝናብ ውኃ ፍሳሽና ሌሎች የህንፃ እድሳት ሥራዎችን ለማሠራት ይፈልጋል፡፡

Consortium-of-Christian-Relief-and-Development-Associations-logo

Overview

  • Category : Construction Service & Maintenance
  • Posted Date : 03/05/2022
  • Phone Number : 0114390322
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 03/18/2022

Description

የህንፃ ጥገና የጨረታ ማስታወቂያ

የክርስቲያን በጎ አድራጎትና ልማት ማህበራት ህብረት CCRDA ከ 400 በላይ አባላት ያሉትና ከ47 ዓመታት በላይ በልማትና በጎ አድራጎት ሥራ ላይ በማገልገል ላይ የሚገኝ ድርጅት ነው፡፡

ድርጅቱ የራሱ የቢሮ ህንፃ የዝናብ ውኃ ፍሳሽና ሌሎች የህንፃ እድሳት ሥራዎችን ለማሠራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የጥገናውን ሥራ ለመሥራት የሚፈልግ ቢያንስ ደረጃው አምስት የሆነ የግንባታ ባለሞያ ጨረታውን መወዳደር ይችላል፡፡

በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች፤

  1. የግብር ከፋይ (Tin No) ቅጂ
  2. የቫት ተመዝጋቢ የምስክር ወረቀት ቅጂ
  3. የታደሰ የሥራ ፈቃድ ቅጂ ማያያዝ አለባቸው

ለመጫረት የሚፈልጉ የሕንፃ ሥራ ባለሞያዎች በድርጅቱ ቢሮ ቁጥር 103 በመቅረብ የማይመለስ ብር 100.00 በመክፈል የሥራዎቹን ዝርዝር የያዘና ዋጋ የሚሞሉበትን ሰነድ ገዝተው ሥራዎቹን በአካል ይመለከታሉ፡፡ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውሰጥ የሚሠሩበትን ዋጋ በመሙላት ያላቸውን የሥራ ልምድ ማረጋገጫና ለሥራው ዋስትና የሚሆን ብር 10,000.00 በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ በታሸገ ኢንቨሎፕ በድርጅቱ ቢሮ ቁጥር 304 ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

የክርስቲያን በጎ አድራጎትና የልማት ማህበራት ህብረት የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 የክርስቲያን በጎ አድራጎትና የልማት ማህበራት ህብረት

     አድራሻ፤ ቃሊቲ ከአሽከርካሪዎችና ሜካኒኮች ማሰልጠኛ ማዕከል ፊት ለፊት

ስልክ 0114-390322 ወይም 0114-393393