የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለመከላከያ ዋና መስሪያቤት ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውሉ Logo አቅርቦትና ገጠማ አስመልክቶ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
Overview
- Category : Graphic Designs & Printing
- Posted Date : 03/05/2022
- E-mail : INFO@dce-et.com
- Phone Number : 0114403434
- Source : Reporter
- Closing Date : 03/26/2022
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር DCE/OI/23/2022
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለመከላከያ ዋና መስሪያቤት ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውሉ Logo አቅርቦትና ገጠማ አስመልክቶ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩ፤ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ የታደሰ ታክስ ክሊራንስ እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚያቀርቡት ገንዘብ በተጫራቾች መመሪያ 7.3 እና 7.4 በተጠቀሰው መሠረት መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰአት ወሎ ሰፈር አካባቢ በሚገኘው የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዋና መ/ቤት የግዥ የሥራ ሂደት ኬዝ ቲም ቢሮ መግዛት ይችላል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በጨረታው ሠነዱ በተጠቀሰው ብዛት እና እስፔሲፊኬሽን መሠረት መሆን ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳሩበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ መጋቢት 17/2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው መጋቢት 17/2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ 4፡15 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡– የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ
የቀጥታ ስልክ ቁጥር 0114-40-34-34
ማዞሪያ 0114-42-22-70/71/72
E-mail አድራሻ Info@dce-et.com
የድህረ ገፅ አድራሻ www.dce-et.com
ፖ.ሳ.ቁ 3414 ፋክስ ቁ. 0114-40-04-71/0114-42-07-46
ወሎ ሰፈር የቀድሞው ኖሬላ ግቢ