መከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለቃሊቲ I አፓርትመንት ግንባታ ፕሮጀክት (17-02B) 5,800.36M3 እንዲሁም ለቃሊቲ II አፓርትመንት ግንባታ ፕሮጀክት (17-03B) 4,374.55M3 ጥራቱን የጠበቀ ለግንባታ ግብአት የሚሆን አሸዋ በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

Defence-Construction-Enterprise-2

Overview

 • Category : Purchases
 • Posted Date : 03/05/2022
 • Phone Number : 0118350773
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 03/22/2022

Description

በድጋሜ የወጣ የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር DCE/17-03/02B/40/03/2022

ድርጅታችን መከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለቃሊቲ I አፓርትመንት ግንባታ ፕሮጀክት (17-02B) 5,800.36M3 እንዲሁም ለቃሊቲ II አፓርትመንት ግንባታ ፕሮጀክት (17-03B) 4,374.55M3 ጥራቱን የጠበቀ ለግንባታ ግብአት የሚሆን አሸዋ በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን ከፕሮጀክቱ ቢሮ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 14 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

በዚህም መሰረት ተጫራቾች፡-

 1. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው እና ተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፤
 2. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በታሸገ ኢንቨሎፕ የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ዘውትር በሥራ ሰዓት እስከ መጋቢት 13/2014 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
 3. ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በፕሮጀክታችን ትክክለኛ ስም ‘Defense Construction Enterprise Army Foundation Apartment Project (Kality 2) (17-03B)’ በባንክ በተረጋገጠ ‘CPO’ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስያዝ ይኖርበቸል፤
 4. ጨረታው በዕለቱ መጋቢት 13/2014 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፕሮጀክቱ ቢሮ ይከፈታል፡፡ በዚህም መሰረት ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን ሀይሌ ጋርመንት አካባቢ ከሚገኘው ሃዮንዳይ ሞተርስ ወረድ ብሎ ወይም ቃሊቲ ገብርኤል ፊት ለፊት ወረድ ብሎ በልዩ ስሙ ጨሬ ሰፈራ የባጃጅ ተራ በሚገኘው ፕሮጀክታችን  ቢሮ መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን ፡፡
 5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ሲያስገቡ የአሸዋውን ናሙና ይዘው መቅረብ አለባቸው፡፡
 6. ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ ፡- አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 7 ጨሬ ሰፈራ ባጃጅ ተራ ፡፡

ለበለጠ መረጃ፡-   በስልክ ቁጥር፡- +251118350773