ጎላጉል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግል/ማህበር አዳዲስ የአዋቂ የወንድና የሴት አልባሳትና ጫማዎች፣ የህፃናት አልባሳትና ጫማዎች እንዲሁም ሌሎች ተጓዳኝ እቃዎች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

Gollagul-logo-reportertenders

Overview

 • Category : Other Sale
 • Posted Date : 03/05/2022
 • Phone Number : 0116900078
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 03/15/2022

Description

ጎላጉል ትሬዲንግ ኃላ.የተ.የግ.ማህበር

አዳዲስ የአዋቂ የወንድና የሴት አልባሳትና ጫማዎች እንዲሁም የህፃናት አልባሳትና ጫማዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ የወጣ ማስታወቂያ

ጎላጉል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግል/ማህበር አዳዲስ የአዋቂ የወንድና የሴት አልባሳትና ጫማዎች፣ የህፃናት አልባሳትና ጫማዎች እንዲሁም ሌሎች ተጓዳኝ እቃዎች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም፡-

 1. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት በጎላጉል ታወር 12ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው ገንዘብ ቤት የማይመለስ ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላል፡፡
 2. ለጨረታ የቀረቡትን አልባሳት እና ሌሎች ተጓዳኝ እቃዎች የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ጎላጉል ታወር በሚገኘው የድርጅቱ ህንፃ 1ኛ ፎቅ ሱቅ ቁጥር 115 ከየካቲት 27 ቀን 2014ዓ.ም እስከ መጋቢት 6 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ባሉት የስራ ቀናት በስራ ሰዓት በአካል ቀርበው መመልከት ይችላሉ፡፡
 3. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ 10% ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ መጋቢት 6 ቀን ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ ጎላጉል ታወር ላይ በሚገኘው የሰው ኃይልና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 1102 ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 4. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት በጎላጉል ታወር 11ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 1102 መጋቢት 6 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ በ9፡15 ሰዓት ይከፈታል፡፡
 5. በተ/ቁ 4 በተገለፀው መሰረት በቂ የዋስትና ማስከበሪያ (CPO) ያላስገቡ ተጫራቾች ከጨረታው ይሰረዛሉ፡፡
 6. የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያው ለአሸናፊዎች ከሚከፍሉት ዋጋ የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊዎች የጨረታው ውጤት እንደታወቀ በ10 ቀናት ውስጥ ያስያዙት የጨረታ ዋስትና (CPO) ይመለስላቸዋል፡፡
 7. አሸናፊው ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በ5 ቀናት ውስጥ አጠቃሎ በመክፈል ርክክብ መፈፀም አለበት፡፡ ሆኖም በተጠቀሰው ቀን ያሸነፈበትን ገንዘብ አጠቃሎ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ያስያዘው ገንዘብ ተመላሽ አይደረግለትም፡፡
 8. መስሪያ ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡-

22 ማዞሪያ ጎላጉል ታዎር

ስልክ ቁጥር 0116900078/0116900178 ቢሮ ቁጥር 1102

የመልእክት ሳጥን ቁጥር 26269 አዲስ አበባ ኢትዮጵያ