ሕብረት ባንክ አዲስ አበባ ከተማ፣ በልደታ ክ/ከተማ፣ በወረዳ 9 ሕንፃ ውስጥ የሚገኙ ውስን ክፍሎችን ለቢሮ እና ለንግድ አገልግሎት እንዲውሉ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡

hibret-bank-done-logo-reportertenders-1

Overview

 • Category : House & Building Rent
 • Posted Date : 03/05/2022
 • Phone Number : 0114704172
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 03/22/2022

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር፡ ሕባ/012/2014

ሕብረት ባንክ አዲስ አበባ ከተማ፣ በልደታ ክ/ከተማ፣ በወረዳ 9 ሰንጋ ተራ አካባቢ አዲስ ባስገነባው የዋናው መስሪያቤት ሕንፃ ውስጥ የሚገኙ ውስን ክፍሎችን ለቢሮ እና ለንግድ አገልግሎት እንዲውሉ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ኪራይ ፈላጊዎች ከዚህ በታች በተገለፀው መሠረት የጨረታ ሰነዱን በመግዛት የመጫረቻ ሰነድ ሊያቀርቡ ይችላሉ፡፡

 1. ተጫራቾች ይህ ጨረታ ለመጀመሪያ ጊዜ በጋዜጣ ከወጣ ከ2 ቀናት በኋላ ማለትም ከየካቲት 30 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ መጋቢት 12 ቀን 2014 ዓ.ም. የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ) በአቅራቢያ በሚገኙ የሕብረት ባንክ ቅርንጫፍ በሂሳብ ቁጥር IN0403007 በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
 2. የጨረታ ሰነዱን በልደታ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 9 ሰንጋ ተራ አካባቢ በሚገኘው የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ሕንፃ 16ኛ ፎቅ ሕንፃ አስተዳደርና ጥገና ዋና ክፍል በመገኘት መግዛት ይቻላል፡፡
 3. ለጨረታ የቀረቡትን ክፍሎች ለመጎብኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ጨረታው ክፍት ሆኖ በሚቆይበት ማለትም ከየካቲት 27 ቀን 2014 ዓ.ም. እስከ መጋቢት 12 ቀን 2014 ዓ.ም. ውስጥ ሰኞ፣ ዕሮብ እና አርብ ከጠዋቱ 3፡00 – 10፡00 ሰዓት ከላይ በተገለፀው አድራሻ በመገኘት ማየት ይችላሉ፡፡
 4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዱን ሞልተው ከማስገባታቸው በፊት በጨረታ ሰነዱ ላይ የተካተተውን የተጫራቾች መመሪያ በደንብ ማየት ይኖርባቸዋል፡፡
 5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) በጨረታው አሸናፊ ሆነው ክፍሉን/ወለሉን ቢከራዩ የሚከፍሉትን የአንድ ወር ኪራይ አንድ አራተኛ (25%) በባንክ የክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) የጨረታ ሰነዱን ሲያቀርቡ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
 6. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚያስይዙትን የባንክ የክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) የሚያሰሩት ከሕብረት ባንክ ውጪ በሆኑ በማንኛውም ባንኮች መሆን አለበት፡፡
 7. እያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ መቅረብ አለበት፡፡
 8. ተጫራቾች ለጨረታው አስፈላጊ የሆኑ ሰነዶችን በማሟላት ልደታ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 9፣ ሰንጋ ተራ አካባቢ በሚገኘው የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ሕንፃ 16ኛ ፎቅ ሕንፃ አስተዳደርና ጥገና ዋና ክፍል በሚገኝ የጨረታ ማስገቢያ ሳጥን ውስጥ መጋቢት 8፣ 9 እና 12 ቀን 2014 ዓ.ም. እስከ ከቀኑ 10፡30 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡
 9. ጨረታው መጋቢት 13 ቀን 2014 ዓ.ም. ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ባንኩ ዋና መስሪያ ቤት አስራ ሶስተኛ /13ኛ/ ፎቅ ላይ በሚገኘው የስብሰባ አዳራሽ ተጫራቾች/ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
 • በጨረታ ሰነዱ ላይ ባለው የተጫራቾች መመሪያ መሠረት ያልቀረበ የመጫረቻ ሰነድ/ተጫራች ከውድድር ሊሰረዝ ይችላል፡፡
 • ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 470 41 72 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

ሕብረት ባንክ

በሕብረት እንደግ!!