ፍቅር ለህጻናትና ቤተሰብ ልማት በጎ አድራጎት ድርጅት ለሚደግፋቸዉ ትምህርት ቤቶች 10 (አስር) ኮምፒዩተሮችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

love-for-children-logo

Overview

 • Category : Computer Purchase
 • Posted Date : 03/05/2022
 • E-mail : loveforchildrenfdco@gmail.com
 • Phone Number : 0113213192
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 03/14/2022

Description

ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ ጨረታ

ፍቅር ለህጻናትና ቤተሰብ ልማት በጎ አድራጎት ድርጅት  መንግስታዊ ያልሆነ ሀገር በቀል የልማት ድርጅት ሲሆን ከቻይልድ ፈንድ ኢትዮጵያ ጋር በአጋርነት የሚሰራ ድርጅት ነዉ፡፡ ድርጅታችን ለሚደግፋቸዉ ትምህርት ቤቶች 10 (አስር) ኮምፒዩተሮችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ የኮምፒዩትሩ ዓይነትና ዝርዝር መረጃ በሚከተለዉ መልኩ ቀርቧል፡፡

DELL Optiplex 3040 Desktop computer specifications

 • Windows 10 pro , Core i3
 • Memory – 8 GB, 1 x 8 GB, DDR4, 2666 MHz
 • Hard Drive Options (internal) – Hard Disk Drives: up to 1TB
 • Speed – 1600 MHz

በመሆኑም ተጫራቾች፡

 1. በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ
 2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸዉና ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
 3. ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ሰባት (7) ቀናት ማለትም ከ የካቲት 28/2014 ዓም ጀምሮ ሰነዳቸዉንና ማስረጃቸዉን የድርጅቱን ማህተም በማስቀመጥና በፖስታ በማሸግ በድርጅቱ ጽ/ቤት በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
 4. ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በስምንተኛው ቀን ሰኞ ከጠዋቱ በ 4፡30 ላይ በግልጽ ይከፈታል
 5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ በተመሰከረለት የክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል
 6. ተጫራቾች በጨረታዉ ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከጨረታዉ ሰነዳቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ
 7. ጨረታ ሳጥኑ ከተዘጋ በኋላ የሚመጣ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
 8. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታዉን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ
 9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የሚያስገቡት የድርጅቱ ጽ/ቤት በሚገኝበት አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ከመካኒሳ ወደ ቆሬ በሚወስደዉ መንገድ ወረዳ ሁለት ወጣት ማዕከል ፊት ለፊት በሚገኘዉ የቸሻየር ፋዉንዴሽን ግቢ ዉስጥ በሚገኘዉ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ይሆናል፡፡
 • ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ተከፍቶ ውሳኔ ይሰጥበታል፡፡
 1. ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ንብረቶች በጨረታ ሰነዱ በተቀመጠው አግባብ በራሳቸው ወጪ የድርጅታችን ቢሮ ድረስ ገቢ ማድረግ አለባቸው፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡ 011 321 31 92 / 011 321 10 27 ወይም በሞባይል ቁጥር 0911 12 13 37 መደወል ይችላሉ

በኢሜል፡ loveforchildrenfdco@gmail.com ይጠይቁ፡፡