ኢንተር ኤይድ ፍራንስ ግብረሰናይ ድርጅት ሲገለገሉባቸው የነበሩ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

Inter-Aide-Ethiopia-logo

Overview

 • Category : Vehicle Sale
 • Posted Date : 03/10/2022
 • Phone Number : 0115159914
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 04/06/2022

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ኢንተር ኤይድ ፍራንስ ግብረሰናይ ድርጅት ሲገለገሉባቸው የነበሩ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ፡-

ተጫራቾች

 1. ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ በወጣ ከ3ኛው ቀን ጀምሮ ንብረቶቹ በሚገኙበት አድራሻ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 7፡30 ሰዓት ድረስ መመልከት ይችላሉ፤
 2. ተጫራቾች የሚገዙትን ንብረት ጠቅላላ ዋጋ 20 በመቶ (20%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) አሰርተው ከዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
 3. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናው ለአሸናፊዎች ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብ ሲሆን ለተሸናፊዎች የጨረታው ውጤት በጸደቀ በ 3 (ሰስት) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ይመለስላቸዋል ፡፡
 4. ተጫራቾች የንብረቶቹን ዝርዝር የያዘው ሠነድ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ በሚለው አምድ /Column/ ሥር የሚገዙበትን ዋጋ በአሃዝና በፊደል ያለ ስርዝ ድልዝ ገልፀው በስም በታሸገ ኤንቬሎፕ/ፖስታ/ ከታች በተገለፀው የድርጅቱ አድራሻ በመምጣት የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ነገር ግን የሚሰጡት ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ከጎኑ በተጫራቹ መፈረም አለበት፡፡
 5. ተጫራቾች ጨረታው በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ሀያ አንድ ተከታታይ የስራ ቀናት /21/ ውስጥ የጨረታውን ሰነድ ማስገባት አለባቸው፡፡ በሀያ አንደኛው ቀን ማለትም መጋቢት 28/2014 ዓ.ም የጨረታ ሰነዱ የሚገባው እስከ 4፡30 ሰዓት ድረስ ብቻ ይሆናል፡፡
 6. አሸናፊ ተጫራቾች ጨረታውን ማሸነፋቸውን ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውሰጥ ገንዘቡን ገቢ በማድረግ በ10 ተከታታይ የሰራ ቀናት ውሰጥ ንብረቱን የመረከብ ግዴታ አለባቸው ይህ ካልሆነ ያስያዙት ገንዘብ ወይም ሲፒ.ኦ. ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል፡፡
 7. ተጫራቾች ከድርጅቱ የንብረቶቹን ዝርዝር መረጃ የያዘ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ የማይመለስ 100 ብር /አንድ መቶ ብር/ እየከፈሉ ማስታወቂያው በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ሀያ አንድ /21/ ተከታታይ የስራ ቀናት ድረስ መግዛት የሚችሉ ሲሆን በሀያ አንደኛው ቀን ሰነዱ የሚሸጠው አስከ ጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ድረስ ብቻ ይሆናል፡፡
 8. የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ሀያ አንድ /21/ የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ በሀያ አንደኛው የስራ ቀን ከጧቱ 4፡30 ሰአት ተዘግቶ በዚያው ቀን 5፡00 ሠዓት ተጫራቾቹ ወይም የተጫራቾቹ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ ይከፈታል፡፡ የጨረታ መክፈቻ ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበዓል ቀነ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል፡፡
 9. ተጫራቾች ስለ አሻሻጡ ዝርዝር ሁኔታ ከጨረታው ሰነዱ ጋር ከተያየዘው የተጫራቾች መመሪያ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
 10. አንድ ተጫራች ሌላው በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፣
 11. ድርጅቱ ለአሻሻጡ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 12. ማንኛውም ወጪ በገዥ የሚሸፈን ይሆናል፡፡

አድራሻ፡ አዲስ አበባ ቂርቆስ ክፍለከተማ ወረዳ 03፡ የቤት ቁጥር 1299 ኢትዮ-ቻይና ጎዳና ከወሎሰፈር ወደ ጎተራ በሚወስደው መንገድ ከአዲሱ የደህንነት መስሪያ ቤት (INSA) ፊት ለፊት ባለው መግቢያ 100 ሜትር ገባ ብሎ፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር ፡ 011-515-99-14 በስራ ሰዓት ብቻ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

ኢንተር ኤይድ ፍራንስ ግብረሰናይ ድርጅት