የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለሰጠው የብድር ገንዘብ አመላለስ በመያዣነት የያዘውን ከዚህ በታች በሠንጠረዥ የተመለከተውን ንብረት በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 1147/2011 በተሰጠው ስልጣን መሠረት በግልፅ ጨረታ /ሐራጅ/ ባለበት ሁኔታ ለመሸጥ ይፈልጋል::
Overview
- Category : Industry & Factory Foreclosure
- Posted Date : 03/10/2022
- Phone Number : 0115245373
- Source : Reporter
- Closing Date : 04/15/2022
Description
የሐራጅ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለሰጠው የብድር ገንዘብ አመላለስ በመያዣነት የያዘውን ከዚህ በታች በሠንጠረዥ የተመለከተውን ንብረት በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 1147/2011 በተሰጠው ስልጣን መሠረት በግልፅ ጨረታ /ሐራጅ/ ባለበት ሁኔታ ለመሸጥ ይፈልጋል::
የተበዳሪው/
የመያዣ ሰጪው ስም |
የንብረት አድራሻ | የንብረት ዝርዝር | የቦታ ስፋት | የሃራጁ መነሻ
ዋጋ (በብር) |
የሐራጁ
ደረጃ |
የሐራጁ ቀንና
ሠዓት |
አለምገነት ንግድና ኢንዱስትሪ ኃ/የተ/የግ/ ማህበር | አዲስ አበባ ከተማ
አስተዳደር፣ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ፣ ወረዳ 12 |
ግንባታዎች፤የመስሪያ ማሽኖች፣ተሽከርካሪዎች፣ጥሬ እቃ እና ተረፈ- ምርቶች |
3,967 ካ.ሜ |
213,818,338.64 (ሁለት መቶ አስራ ሶስት ሚሊዮን ስምንት መቶ አስራ ስምንት ሺህ ሶስት መቶ ሰላሳ ስምንት ብር ከ64/100) |
የመጀመሪያ |
ሚያዝያ 11 ቀን 2014 ዓ.ም
ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት |
ማሳሰቢያ ፤
- ተጫራቾች የሐራጁን መነሻ ዋጋ 25 በመቶ በባንክ ክፍያ ማዘዣ /ሲ.ፒ.ኦ/ ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ፤
- አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በ15 /በአስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ካልከፈለ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል፡፡ በተጨማሪም ንብረቱ ድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ በሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል፡፡
- ሐራጁ የሚካሄደው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው፣ ተበዳሪው እና የሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ተወካዮች ብቻ በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው የንብረት አድራሻ፣ ቀንና ሰዓት ነው:: በሐራጁ ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት የባንክ ክፍያ ማዘዣ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወዲያውኑ ተመላሽ ይደረጋል፡፡
- 15% የተጨማሪ እሴት ታክስና ሌሎች ገዢ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰነ ክፍያዎችን፣ የስም ማዛወሪያ ክፍያን ጨምሮ ገዢው ይከፍላል፤
- አንዳንድ የድርጅቱ ተሽከርካሪዎች፣ማምረቻ መሣሪያዎች፣ወዘተ የጉምሩ ክቀረጥና ታክስ ያልተከፈለባቸው ስለሆኑ ገዢው የቀረጥ ነጻ መብት ሊኖረው አሊያም በመንግስት የሚፈለገውን ቀረጥ ለመክፈል ይገደዳል ::
- ባንኩ ለሽያጭ የቀረቡትን ንብረቶች የሚሸጠው ከተቻለ ሙሉ በሙሉ በጥሬ ገንዘብ ሲሆን አሸናፊው በባንኩ ብድር ፖሊሲ መሠረት አስፈላጊውን መስፈርቶች ካሟላና የፕሮጀክቱን ሥራ የሚያስቀጥል ከሆነ ንብረቱን በከፊል ብድር ለመግዛት መጠየቅ ይችላል:: ነገር ግን በከፊል ብድር ለመግዛት የጨረታ አሸናፊው በራሱ ስም ወይም እራሱ 10%/አስር በመቶ/ ወይም ከዚያ በላይ የአክሲዮን ባለድርሻ የሆነበት የንግድ ማህበር ከግብር፤ከታክስና ከሌሎች ማናቸውም ዕዳዎች ነፃ መሆኑን ከሚመለከታቸው አካላት ማስረጃ በማቅረብ እንዲሁም ምንም ዓይነት የዕዳ ይከፈለኝ ጥያቄ ያልቀረበበት መሆን አለበት፡፡
- ዝርዝር እና ተጨማሪ መረጃን በተመለከተ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ዋና መ/ቤት ታወር ሁለት ሦስተኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የኘሮጀክት ማገገሚያና ብድር ማስመለስ ዳይሬክቶሬት-II በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 011-524-53-73 ደውሎ ማግኘት ይቻላል፡፡ንብረቱን ለመጎበኘት የሚፈልጉም ካሉ ከዳሬክቶሬቱ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ መጐብኘት ይቻላል፤
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ሐራጁን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ