የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት ከውጭ ሀገር የገዛውንና ለተጠቃሚው ማህበረሰብ በተለያዩ ቅርንጫፎቹ በኩል በተመጣጣኝ ዋጋ የሚያሰራጨውን የምግብ ዘይት ከጅቡቲ፤ ከደረቅ ወደቦች እና ከኢንዶዴ ባቡር ጣቢያ በኮንቴነር እና ያለኮንቴነር የሚያጓጉዙ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለአንድ ዓመት በሚቆይ ውል ማሰራት ይፈልጋል፡፡

Ethiopian-Industrial-Inputs-Development-Enterprise-Logo

Overview

  • Category : Transport Service
  • Posted Date : 03/10/2022
  • Phone Number : 0113692647
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 03/21/2022

Description

የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት

የጭነት አገልግሎት ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 017/14

ድርጅታችን ከውጭ ሀገር የገዛውንና ለተጠቃሚው ማህበረሰብ በተለያዩ ቅርንጫፎቹ በኩል በተመጣጣኝ ዋጋ የሚያሰራጨውን የምግብ ዘይት ከጅቡቲ፤ ከደረቅ ወደቦች እና ከኢንዶዴ ባቡር ጣቢያ በኮንቴነር እና ያለኮንቴነር የሚያጓጉዙ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለአንድ ዓመት በሚቆይ ውል ማሰራት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ በጨረታው መካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች፤

  1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ሥራ ፍቃድ፣ የብቃት ማረጋገጫ ሠርተፍኬት፣ የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው የሚያረጋግጥ ክሊራንስ፣ የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሠርተፍኬት ያላቸው መሆን ይገባቸዋል፡፡
  2. ለጨረታው የተዘጋጀውን ዝርዝር የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ቢስ መብራት አካባቢ ከሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስርያ ቤት የኢንዱስትሪ ውጤቶች ግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ  ማዘዣ/ሲ.ፒ.ኦ ብቻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

3.1 ከዚህ ቀደም ለሌላ ጨረታ የተያዘ ሲ.ፒ.ኦን ለዚህ ጨረታ እንዲያዝ ማድረግ አይቻልም፡፡

3.2 ተጫራቾች በጨረታ መመሪያው ላይ የሚቀመጡትን ህጎች በሙሉ በማክበር ግዴታ አለባቸው፡፡

  1. የጨረታ መወዳደሪያ ዋጋቸውንና ከላይ ከተጠቀሱት ህጋዊ ሠነዶች ጋር በታሸገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦሪጅናል እንዲሁም አንድ ኮፒ በማድረግ እስከ መጋቢት 12 ቀን 2014 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይችላሉ፡፡
  2. ጨረታው በተመሳሳይ ቀን (መጋቢት 12 ቀን 2014 ዓ.ም) ከረፋዱ 4፡10 ተጫራቾች በተገኙበት ይከፈታል፡፡

ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ እንዲሁም ለማህበረሰቡ ይጠቅማሉ ያላቸውን ውሳኔዎች የመወሰን መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0113-69-26-47/69-24-39