የድር ተራ አክሲዮን ማህበር ከአክሲዮን ማህበሩ የሚሰበሰበውን ገቢና ወጪ ሂሳቦችን የውጭ ኦዲተር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ የሶስት አመት ኦዲት ማሰራት ይፈልጋል፡፡

Overview

 • Category : Auditing Related
 • Posted Date : 03/13/2022
 • Phone Number : 0112139245
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 03/18/2022

Description

የድር ተራ አክሲዮን ማህበር

የውጭ ኦዲተር የጨረታ ማስታወቂያ

የድር ተራ አክሲዮን ማህበር ከአክሲዮን ማህበሩ የሚሰበሰበውን ገቢና ወጪ ሂሳቦችን የውጭ ኦዲተር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ የሶስት አመት ኦዲት ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ከዚህ በታች የተገለፀውን የጨረታ መመሪያ መሰረት በማድረግ ተጫራቾች እንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል፡፡

 1. ተጫራቾች በጨረታው ለመካፈል ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን (2013) ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
 2. የኦዲት ሥራ ለመስራት ፕሮፌሽናል ፍቃድ ያላቸው መሆን አለባቸው
 3. የተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ እና TIN NO ያላቸው የሆኑና ለዚህ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
 4. ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን በትክክል ፅፎ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
 5. ጨረታው መጋቢት 5 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ መጋቢት 9 ቀን 2014 ዓ.ም. ለ5 የሥራ ቀን ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን በ10/7/2014 ከጠዋቱ 4፡00 ይዘጋል፡፡
 6. ጨረታውም 10/7/2014 ተጫራቾቻቸው ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በማህበሩ ጽ/ቤት ከጠዋቱ 4፡15 ይከፈታል፡፡
 7. ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 • የምዝገባ ቦታ፡- መርካቶ ጣና የገበያ ማዕከል አጠገብ በሚገኘው አክሲዮን ማህበሩ ባሰራው ሕንፃ ውስጥ 4ተኛ ፎቅ በሚገኘው የአክሲዮን ማህበሩ ጽ/ቤት

ስልክ ቁጥር 0112139245/0112138967

® ማሳሰቢያ፡- አመልካቾች ለምዝገባ ሲቀርቡ የንግድ ፍቃድ ፎቶ ኮፒ ይዘው መምጣት ይጠበቅባቸዋል፡፡