አዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ. ለተለያዩ አገልግሎቶች ሲጠቀምባቸው የነበሩትን የአልሙኒየምና ካውንተር ፍራሽ፣ የጥበቃ ቤቶች፣ የተለያዩ ያገለገሉ የመኪና መለዋወጫዎች እና ጂፕሰም ቦርድ ባለበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

Awash-Bank-logo-Reportertenders-2

Overview

 • Category : Other Sale
 • Posted Date : 03/13/2022
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 03/24/2022

Description

ያገለገሉ ንብረቶችን የጨረታ ማስታወቂያ

አዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ. ለተለያዩ አገልግሎቶች ሲጠቀምባቸው የነበሩትን የአልሙኒየምና ካውንተር ፍራሽ፣ የጥበቃ ቤቶች፣ የተለያዩ ያገለገሉ የመኪና መለዋወጫዎች እና ጂፕሰም ቦርድ ባለበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡   በመሆኑም በጨረታው ላይ መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ከታች የተዘረዘሩትን ቅድመ ሁኔታዎችን በማሟላት በጨረታው ላይ መሳተፍ የሚቻል መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን፡-

 1. ስለ ጨረታው አፈጻጸም ዝርዝር መረጃ የማይመለስ ብር00(አንድ መቶ ብር) በየትኛውም የአዋሽ ባንክ ቅርንጫፍ በሂሣብ ቁጥር 01540000544500 በተጫራቹ ስም ገቢ በማድረግ ደረሰኙን አዋሽ ባንክ ባልቻ ሳፎ ሕንጻ 9ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 9/03 በማቅረብ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መጋቢት 15 ቀን 2014 ዓ.ም. ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዱን መግዛትና ማስገባት ይችላሉ፣
 2. እያንዳንዱ ተጫራች ለሚጫረትባቸው ንብረቶች ላይ የሚሰጠውን የመወዳደሪያ ዋጋ ¼ የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ሰነድ (CPO) በአዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ አክስዮን ማህበር ስም አሰርቶ ማስገባት ይኖርበታል፣
 3. ያለ ጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፣
 4. የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈበት ዋጋ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ(VAT) 15% በተጨማሪነት ይከፍላል፣
 5. ንብረቶቹ በየዘርፋቸው አሸዋ ሜዳ እና ጃክሮስ በሚገኘው የባንኩ መጋዘን በአካል ቀርቦ በጨረታው ሰነድ ላይ በወጣው ፕሮግራም መሰረት መጐብኘት ይቻላል፣
 6. ጨረታው መጋቢት 15 ቀን 2014 ዓ.ም. ከቀኑ 4፡10 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባልቻ ሳፎ ሕንጻ 9ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 9/03 ውስጥ ይከፈታል፣ ከጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት በኋላ የሚቀርቡ የመወዳደሪያ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም፣
 7. የጨረታው አሸናፊ የጨረታው ውጤት ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የሥራ ቀናት ውስጥ ክፍያ ፈጽሞ ንብረቶቹን መረከብ ይኖርበታል፡፡ ይህ ካልሆነ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ በማድረግ ጨረታው ይሰረዛል፣
 8. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡