የኢትዮጵያ ልማት ባንክ መነሻ ግምታቸው ብር 152,417.58/ አንድ መቶ ሃምሳ ሁለት ሺ አራት መቶ አስራ ሰባት ብር ከ58/100 ሳንቲም/ የሆኑ የተለያየ መጠን ያላቸው ሥራ ላይ ያልዋሉ ጐማዎች እና ከመነዳሪዎች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

Development-bank-of-Ethiopia-logo-4

Overview

 • Category : Tyre & Battery
 • Posted Date : 03/13/2022
 • Phone Number : 0115506018
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 04/16/2022

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ መነሻ ግምታቸው ብር 152,417.58/ አንድ መቶ ሃምሳ ሁለት ሺ አራት መቶ አስራ ሰባት ብር ከ58/100 ሳንቲም/ የሆኑ የተለያየ መጠን ያላቸው ሥራ ላይ ያልዋሉ ጐማዎች እና ከመነዳሪዎች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

 • ተጫራቾች የጐማዎቹን እና ከነመነዳሪዎቹን ዝርዝር የያዘውን የጨረታ ሰነድ በባንኩ ሁለተኛ ታወር አምስተኛ ፎቅ ንብረትና ፋሲሊቱ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት ቢሮ መውሰድ ይችላሉ፡፡
 • ተጫራቾች የሚገዙበትን ዋጋ በመጥቀስና የታደሰ የነዋሪነት መታወቂያ በማያያዝ በሰም በታሸገ ኤንቨሎኘ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣ ከሶስተኛው ቀን ጀምሮ የኢትዮዽያ ልማት ባንክ ዋናው መስሪያ ቤት ሁለተኛ ታወር መግቢያ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እስከ ሚያዝያ 6 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡
 • የጨረታ ሳጥኑ ሚያዝያ 6 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ታሽጐ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሚያዝያ 6 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 8፡05 ይከፈታል፡፡
 • በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ በቅድሚያ መነሻ ዋጋውን 25% /ሃያ አምስት በመቶ/ በገንዘብ ክፍያ ማዘዣ /ሲፒኦ/ ማስያዝ አለበት፡፡
 • አሸናፊው ያስያዘው ገንዘብ ከግዢው ዋጋ ጋር ሲታሰብለት ለተሸነፋት ያስያዘት ገንዘብ ወዲያዉኑ ይመለስላቸዋል፡፡
 • የጨረታው አሸናፊ ማሸነፋ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 10 ተከታታይ ቀናት የገዛበትን ገንዘብ ሙሉ በሙሉ ከፍሎ ጐማዎቹ መረከብ ይኖርበታል፡፡ ይህ ካልሆነ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ሙሉ ለሙሉ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፡፡
 • ገዢው በገዛበት ዋጋ ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ 15% /አስራ አምስት በመቶ/ መክፈል ይጠበቅበታል፡፡
 • ተጨማሪ መረጃ የኢትዮዽያ ልማት ባንክ ስልክ ቁጥር 011551-11-88 የውስጥ መስመር ቁጥር 386 ወይም በቀጥታ መስመር 0115506018 ደውሎ ማግኘት ይቻላል፡፡
 • ተጫራቾች ጐማዎቹን እና ከመነዳሪዎቹን መመልከት ከፈለጉ የኢትዮዽያ ልማት ባንክ መጋዘን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር ረቡዕ ከቀኑ 8፡00-10፡00 ሰዓት በአካል በመገኘት መመልከት ይችላሉ፡፡
 • ባንኩ ስለ ጐማዎቹ አሻሻጥ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ