የኒያላ ኢንሹራንስ አ.ማ. ከዚህ በታች የተገለጹትን አክሲዮኖች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

Nyala-Insurance-logo

Overview

 • Category : Other Sale
 • Posted Date : 03/13/2022
 • Phone Number : 0116626667
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 03/28/2022

Description

ኒያላ ኢንሹራንስ አ.ማ.

የአክሲዮን ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

የኒያላ ኢንሹራንስ አ.ማ. ከዚህ በታች የተገለጹትን አክሲዮኖች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

የአክሲዮኖቹ ዝርዝር መግለጫ

ለጨረታ የቀረቡ አክሲዮኖች መለያ ቁጥር የአክሲዮኖች ብዛት የአንዱ አክሲዮን የጨረታ መነሻ ዋጋ የአክሲዮኖቹ ጠቅላላ የጨረታ መነሻ ዋጋ
003 31,840 ብር 1,000 ብር 31,840,000.00

በመሆኑም ተጫራቾች፡-

 1. በጨረታው መሳተፍ የሚችሉት ዜግነታቸው ኢትዮጵያዊ የሆኑ ግለሰቦች ፣ የንግድ ድርጅቶች እና በሀገሪቱ ሕግ መሰረት የፋይናንስ ተቋማት አክሲዮኖችን እንዲገዙ ወይም እንዲይዙ የተፈቀደላቸው እና ሌሎች መስፈርቶችን የሚያሟሉ አካላት መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
 2. አክሲዮኖችን በመነጣጠል ዋጋ ማቅረብ አይቻልም::
 3. ተጫራቾች በኩባንያው የተዘጋጀውን የጨረታ ዝርዝር መመሪያና የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 4 ሚኪሊላንድ ጎዳና ከሚገኘው የኩባንያው ዋና መ/ቤት ‹‹ፕሮቴክሽን ሀውስ›› የሪሶርስ ማኔጅመንት መምሪያ ቢሮ ቁጥር 307 በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
 4. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በመሙላት እና ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን የሚጫረቱበትን ዋጋ 10 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) በማካተት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መጋቢት 19 ቀን 2014 ዓ.ም. ከቀኑ 6፡00 ሠዓት ድረስ ባሉት ቀናት ውስጥ በዋናው መ/ቤት 4ኛ ፎቅ ለዚሁ አላማ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
 5. ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በኩባንያዉ ዋና መ/ቤት መጋቢት 19 ቀን 2014 ዓ.ም. ከቀኑ 9፡00 ሠዓት በይፋ የሚከፈት ይሆናል፤
 6. ኩባንያው ጨረታውን በማንኛውም ጊዜ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ኒያላ ኢንሹራንስ አ.ማ. ዋና መ/ቤት

አ.አ ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 4 ሚኪ ሊላንድ ጎዳና  ፕሮቴክሽን ሐዉስ

ሥልክ 011-6-62 66 67 / 62 67 07

ኢ-ሜል፡ nisco@nyalainsurancesc.com