የበጌሚድር አፓርትመንት ሞል እና ሪልስቴት አ.ማ ከአባላት በተሰበሰበ በጀት በ2014ዓ/ም በጎንደር ከተማ ባለሶስት ቤዝመንት ሞል እስከ አንደኛ ወለል የመዋቅር (ስተራክቸር) ስራ የእጅ ዋጋ በዘርፉ የተሰማሩ GC/BC-ደረጃ 3 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ስራ ተቋራጮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል ፡፡

Overview

 • Category : Construction Service & Maintenance
 • Posted Date : 03/30/2022
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 04/15/2022

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

     የበጌሚድር አፓርትመንት ሞል እና ሪልስቴት አ.ማ ከአባላት በተሰበሰበ በጀት በ2014ዓ/ም በጎንደር ከተማ ቀበሌ 18 ማራኪ ክ/ከተማ ባለሶስት ቤዝመንት ሞል እስከ አንደኛ ወለል የመዋቅር (ስተራክቸር) ስራ የእጅ ዋጋ በዘርፉ የተሰማሩ GC/BC-ደረጃ 3 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ስራ ተቋራጮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል ፡፡

በመሆኑም ማናኛውም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟላ ሁሉ በጨረታው እንድትወዳደሩ ተጋብዛችኋል ፡፡

በመሆኑም ተጫራቾች ፡-

 1. በዘርፉ የወጣና የዘመኑ የታደሰ ንግድ ስራ ፈቃድ ኮፒ ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ኮፒ ፣የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፊኬት ኮፒ ፣ በአቅራቢነት በኤጀንሲው ድረ – ገጽ የተመዘገቡ በማንኛውም የመንግስት ግዥ ጨረታ እንዲሳተፉ በሃገር ውስጥ ገቢ ባለስልጣን / ከሚመለከተው የገቢዎች መስሪያ ቤት / የተሰጠ የድጋፍ ደብዳቤ ኮፒ፣ የማጭበርበር ድርጊት ላለመፈጸሙ ቃል የገቡበት ቅጽ ሞልተው ፣ ፈርመው እና በድርጅታቸው ማህተም አረጋግጠው ዋናውን ማቅረብ አለባቸው ፡፡
 2. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆን ብር 500,000.00 /አምስት ሞ ሽህብር / በጥሬ ገንዘብ ወይም ከታወቀ ባንክ በሚሰጥ ሲ.ፒ.ኦ. ወይም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ቼክ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በበጌሚድር አፓርትመንት ሞል እና ሪልስቴት አ.ማ. ስም አስርተው ማቅረብ አለበት ፡፡በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትናው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ቢያንስ ከ18 ቀን በታች መሆን የለበትም ፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናው በቴክኒካል ሰነዱ ውስጥ መካተት ይኖርበታል ፡፡
 3. ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ኮፒ ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ኮፒ ፣የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፊኬት ኮፒ ፣ በአቅራቢነት ድረ – ገጽ ምዝገባ ሰርተፊኬት ኮፒ ፣ የገቢዎች ክሊራንስ ፣ ለማጭበርበር ፎርም ፣ የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ( CPO ) እና ሌሎች የቴክኒካል ሰነዶችን በአንድ ፖስታ እንዲሁም የዋጋ መወዳደሪያ ሰነዳቸውን ኦርጅናል ኮፒ በማለት በተለያየ ፖስታ በማሸግና በማያሻማ ሁኔታ በጀርባው ላይ ኦርጅናል እና ኮፒ በሚል በጽሁፍ በማመላከትና በድርጅታቸው ማህተም በማረጋገጥ ማቅረብ አለባቸው ፡፡
 4. ሁሉም ሦስት ፖስታዎች በአንድ ትልቅ ፖስታ ተጠቃለው መታሸግና በድርጅቱ ማህተም አረጋግጠው ማሰገባት አለባቸው ፡፡
 5. ማንኛውም ተጫራች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በበጌምድር አፓርትመንት፤ሞል እና ሪልስቴት አ.ማ ቢሮ ቁጥር 202 ዘወትር በሥራ ሰዓት በመምጣት የማይመለስ ብር 1000.00 / አንድ ሺህ ብር / በመክፈል መውሰድ ይቻላል ፡፡
 6. ተጫራቾች የጨረታ መወዳደሪያ ሰነዳቸውን በጌሚድር አፓርትመንት ሞል እና ሪልስቴት አ.ማ ቢሮ ቁጥር 202 ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ይህ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር እስከ 15ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ስዓት ድረስ ማስገባት ይችላሉ ፡፡ ጨረታውም ታዛቢዎችና ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ዕለት 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በእለቱ 4፡10 ሰዓት ጀምሮ በበጌ ምድር አፓርትመንት፤ሞል እና ሪልስቴት አ.ማ ቢሮ ቁጥር 202 ይከፈታል ሆኖም 15ኛው ቀን የህዝብ ወይም የሃይማኖት በዓል ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት እና ቦታ ይከፈታል ፡፡
 7. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ቢያንስ 15 ቀን ድረስ ፀንቶ መቆየት አለበት ፡፡
 8. ማንኛውም ተጫራች ዋጋ ሲሞላ ቫትንና ሌሎች ታክስ እንዲሁም የትራስፖርት ዋጋ ጨምሮ መሆን አለበት ፡፡ የታክስ ሁኔታ ያልተገለጸ ከሆነ የተሞላው ዋጋ ማንኛውንም የመንግስት ታክስና ወጭን አካቶ እንደሞላ ተደርጎ ይቆጠራል፡፡
 9. ማንኛውም ተጫራች በሌላ ዋጋ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
 10. ተጫራቾች የቴክኒካል ሰነድ ማስረጃቸውን በመደበኛ የተጫራቾች ሰነድ መሰረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል ፡፡
 11. የግንባታው መጠን በሰነዱ ላይ በተገለጸው መሰረት በ20 % ሊጨምር ሆነ ሊቀንስ ይችላል፡፡
 12. ተጫራቾች ተጨማሪ ተያያዥ ማስረጀዎችን በመደበኛ የተጫራቾች ሰነድ ( SBD ) ማግኘት ይችላሉ ፡፡
 13. የበጌምድር አፓርትመንት ሞል እና ሪልስቴት አ.ማ የተሸለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ፡፡

በጌምድር አፓርትመንት ሞል እና ሪልስቴት አ.ማ

ጨረታው የሚዘጋበት ቀንና ሰአት              15ኛው ቀን ከጠዋት 4፡00 ስዓት

ጨረታው የሚከፈትበት ቀንና ሰአት              15ኛው ቀን ከጠዋት 4፡10 ስዓት