የተባበሩት ብሔራዊ ፔትሮሊየም አክሲዮን ማህበር ያሉትን ተሸከርካሪዎች በጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለጸው ዝርዝር መሠረት ባሉበት ሁኔታ በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

yetebaberut-Beherawi-logo

Overview

 • Category : Vehicle Sale
 • Posted Date : 04/04/2022
 • Phone Number : 0116638577
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 04/19/2022

Description

የተባበሩት ብሔራዊ ፔትሮሊየም አ.ማ.

YETEBABERUT BEHARAWI PETROLEUM S.C.

የጨረታ ማስታወቂያ

የተባበሩት ብሔራዊ ፔትሮሊየም አክሲዮን ማህበር ያሉትን ተሸከርካሪዎች በጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለጸው ዝርዝር መሠረት ባሉበት ሁኔታ በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ተሽከርካሪዎችን መግዛት የሚፈልጉ ሁሉ 22 ማዞሪያ በዘሪሁን ሕንፃ ገባ ብሎ ከ3- ዴይስ (3 days) ኢንተርናሽናል ሆቴል አጠገብ /ሚኪሊላንድ መንገድ/ በሚገኘው የኩባንያው ዋና መስሪያ ቤት በመገኘትና በማየት የሚገዙበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ፖስታ እስከ ሚያዝያ 11 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ በዋና መስሪያ ቤት 2ኛ ፎቅ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ገቢ በማድረግ መጫረት ይችላሉ፡፡

 1. ጨረታው ሚያዝያ 11 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት በኩባንያው ዋና መስሪያ ቤት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ይከፈታል፣
 2. ሌሎች ተጫራቾች በአቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት የተከለከለ ነው፣
 3. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ከዋናው መስሪያ ቤት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፣
 4. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የተሸከርካሪ ዋጋ 10% (አስር በመቶ) በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO)ማስያዝ ይኖርባቸዋል፣
 5. ተሸከርካሪዎቹ ከጨረታው በፊት ማንኛውም ዕዳ ቢኖራቸው በኩባንያው ይሸፈናል፡፡ ከጨረታው በኋላ ያሉትን ማንኛውንም ወጪዎች ገዥው ሙሉ በሙሉ ይሸፍናል፣
 6. የጨረታ አሸናፊዎች በአሸነፉበት ዋጋ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) 15% (አስራ አምስት በመቶ) በተጨማሪነት ይከፍላል፣
 7. አሸናፊዎች የጨረታው ውጤት ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ አስር ቀናት ድረስ ክፍያ ፈጽመው ንብረቶችን ካልተረከቡ የጨረታው ውጤት የሚሰረዝ ሆኖ ከላይ ለጨረታ ማስከበሪያ ያሲያዙት ገንዘብ ለኩባንያው ገቢ ይደረጋል፣
 8. ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ማስታወሻ፡- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0116-63-85-77/80 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡