በላይአብ ሞተርስ ኃ.የተ.የግል ማህበር የተለያዩ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን (Spare parts) በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
Overview
- Category : Spare Parts Sale & Supply
- Posted Date : 04/10/2022
- Phone Number : 0966215183
- Source : Reporter
- Closing Date : 04/19/2022
Description
የመለዋወጫ ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
በላይአብ ሞተርስ ኃ.የተ.የግል ማህበር የተለያዩ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን ማለትም:-
የሲኖ ትራክ (SINO Truck)፤ የኒሳን ዩዲ ( Nissan UD)፤ የፉቶን ዳምፕ ትራክ (Futon Dump Truck) ፤ ዲፋክ 70 ኩንታል (DFAC 70Q)፤ የሎደር (Loader)፤ የኢስካቫተር (Excavator)፤ የሪዮት ኮንትሮል (Riot Control) እና የዳምፐር (Damper) መለዋወጫዎችን (Spare parts) በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ እቃዎቹ አዲስ አበባ እና አዳማ በሚገኘው የድርጅቱ ቅርንጫፍ መስሪያ ቤቶች ይገኛሉ፡፡
ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶችና ግለሰቦችን በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
- ተጫራቾች የታደሰ ፊቃድ፤ የግብር ከፋይ ሰርተፍኬት፤ የቫት ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጫረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100/አንድ መቶ ብር/ በመግዛት ዋጋቸውን በመሙላት ለጫረታው በተዘጋጀው ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው የሚቆየው ጋዜጣው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ7 ተከታታይ የስራ ቀናት ሲሆን በ8ኛው ቀን 4፡00 ተከፍቶ 4፡30 ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሳሪስ ቀይ መስቀል ቢሮ ቁጥር 01 ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የተለያዩ መለዋወጫ እቃዎች ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ )በባንክ በተረጋገጠCPO ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው እቃዎች ድርጅቱ ባወጣው የመነሻ ዋጋ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ሰነድ ከገዙ በኋላ ቃሊቲ ብሔራዊ ት/ቤት ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ መጋዘን በመቅረብ የእቃዎቹን ናሙና በአካል ማየት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት እያንዳንዱ ሰነድ ላይ የድርጅታቸውን ማህተምና ፊርማቸውን ማኖር ይጠበቅባቸዋል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ወይም ግለሰብ ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች ዋጋ ከፍሎ በ15 ቀናት ውስጥ ማንሳት ይኖርባቸዋል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ሌሎች ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
ከላይ በተዘረዘሩት መስፈርት ማሟላት የምትችሉ ተጫራቾች ሰነዱን ቃሊቲ ብሔራዊ ት/ቤት ጀርባ ከሚገኘው የበላይአብ ሞተርስ ቅርንጫፍ መውሰድ ይችላሉ፡፡
አድራሻ
በላይአብ ሞተርስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
ሞባይል ፡-0966 21 51 83/0913 35 13 57
ስልክ ፡- 0114 70 9723
ፋክስ ፡- 0114 70 96 12
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ