የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የጃንሜዳ ስታፍ ኮሌጅ የG+2 ህንፃ ግንባታ ፕሮጀክት (11-09B) ፕሮጀክት ስራ አገልግሎት የሚውል GROUNDING AND POWER CABLE ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡
Overview
- Category : Purchases
- Posted Date : 04/10/2022
- Phone Number : 0118121352
- Source : Reporter
- Closing Date : 04/20/2022
Description
የጨረታ ማስታወቂያ፡-
የጨረታ ቁጥር DCE/JAN/008/2014
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የጃንሜዳ ስታፍ ኮሌጅ የG+2 ህንፃ ግንባታ ፕሮጀክት (11-09B) ፕሮጀክት ስራ አገልግሎት የሚውል DISTRIBUTIONE BOARD & FLOOR STANDING COMBINING COMPARATEMENT IN SHEET STEEL ENCLOSURE WITH LOCABLE DOOR AND CONSISTING & GROUNDING AND POWER CABLE ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡
ስለሆነም፡-
- ተጫራቾች ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚያቀርቡት ገንዘብ በተጫራቾች መመሪያ ተራ ቁጥር 7.3 እና 7.4 በተጠቀሰው መሠረት መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመክፈል ዘወትር በስራ ሰአት ቅዳሜን ጨምሮ ተከታታይ 10 የስራ ቀናት ጃንሜዳ ስታፍ ኮሌጅ (17-06B) ፕሮጀክት የስታፍ ኮሌጅ ቅጥር ግቢ ውስጥ በሚገኘው የፕሮጀክት ገንዘብ ያዥ ቢሮ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች ካታሎግ ፣ ናሙናና የጥራት ማረጋገጫ (Quality Certificate) ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ወይም በጨረታ መክፈቻ ቀን በካታሎጉ ላይ የሚወዳደሩበትን ዕቃ ለይቶ በማመልከት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው ዕቃዎች የ3ኛ ወገን(Authorization) እና ቴክኒካል ሰነድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ ሚያዝያ 12/2014 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ሚያዝያ 12/2014 ዓ/ም ከቀኑ 8፡30 ከሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፕሮጀክቱ ቢሮ ይከፈታል፡፡
- ፕሮጀክቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ
የጃንሜዳ አዣዥነትና ስታፍ ኮሌጅ ፕሮጀክት (17-06B)
የቀጥታ ስልክ ቁጥር ዐ118-95-98-10 ወይም 0118121352