ፊዩቸር ታለንት አካዳሚ ከዚህ ቀጥሎ በሰንጠረዥ የተገለፀውን ተሸከርካሪ በአዋጅ ቁጥር 1147/2011 በተሰጠው ሥልጣንና ውክልና መሠረት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
Overview
- Category : Vehicle Sale
- Posted Date : 04/09/2022
- Phone Number : 0114422640
- Source : Reporter
- Closing Date : 04/27/2022
Description
የመኪና ሽያጭ ጨረታ
ፊዩቸር ታለንት አካዳሚ ከዚህ ቀጥሎ በሰንጠረዥ የተገለፀውን ተሸከርካሪ በአዋጅ ቁጥር 1147/2011 በተሰጠው ሥልጣንና ውክልና መሠረት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
የሰሌዳ ቁጥር | የሻንሲ ቁጥር | የሞተር ቁጥር | የተሸከርካሪ ዓይነት | የጨረታ መነሻ ዋጋ | የጨረታ ቀን |
3-68197አ.አ | LSYHBAAA19K075043 | JM491GCME-E25838 | አውቶቡስ/ሚኒባስ/ | 200,000 | 19/08/2014
ጠዋት 4፡00 ሰዓት |
ማሳሰቢያ፡–
- ተጫራቾች የጨረታውን መነሻ ዋጋ 5% /አምስት በመቶ/ በባንክ ክፍያ ማዘዥ (ሲ.ፒ.ኦ) አሰርተው ጨረታው በሚካሄድበት ዕለት ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው የሚካሄደው በሰንጠረዡ ላይ በተገለፀው ቀንና ሰዓት በትምህርት ቤቱ አዳራሻ ውስጥ ይካሄዳል፡፡
- ከፍተኛ ዋጋ ላልሰጡ ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፡፡ ከፍተኛ ዋጋ ላቀረበ ተጫራች ግን ድርጅቱ ዋጋውን የሚቀበል መሆን አለመሆኑን ከጨረታው በኃላ ባሉት አምስት የስራ ቀናት ውስጥ ለተጫራቹ ያሳውቃል፡፡
- በጨረታው አሸናፊ የሆነ ተጫራች የአሸነፈበትን ዋጋ በ15 ቀን ውስጥ ለድርጅቱ ገቢ ማድረግ ይኖርበታል፡፡
- ከላይ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ገቢ ለማያደርግ አሸናፌ ተጫራች ጨረታው ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ ይደረጋል፡፡
- በተሸከርካሪው ሽያጭ ላይ የተ.እ.ታ የሚታሰብ ሲሆን ተሸከርካሪውን በማስተላለፍ ሂደት ለመንግስት የሚከፈል ታክስና ማንኛውንም ክፍያ ገዢ ይከፍላል፡፡
- ድርጅቱ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- ወሎ ሰፈር ኢትዮ ቻይና መንገድ ወደ ጎርጎሪዮስ ቤተ/ክርስቲያን መውረጃ ካስማ ህንፃ ላይ፡፡
ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥራችን 0114422640/ 0114405902 መደወል የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ድርጅቱ