ወተርኤድ ኢትዮጵያ ለቢሮ አገልግሎት ሲጠቀምባቸው የነበሩትን የተለያዩ የቢሮ ዕቃዎች እንዲሁም አንድ ያገለገለ መኪና ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

water-aid-done

Overview

 • Category : Other Sale
 • Posted Date : 04/11/2022
 • Phone Number : 0116695965
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 04/30/2022

Description

ያገለገሉ ልዩ ልዩ ንብረቶች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር፡ WAE/Used/OB/2022/0001

ዋተርኤድ ኢትዮጵያ በመጠጥ ውሀ ፤ ሳኒቴሽንና ሀይጂን ዙሪያ የሚሰራ አለምዓቀፍ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ሲሆን ፤ በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ ውሀ ሳኒቴሽንና ሀይጂን ስራዎች ላይ ከመንግስት ጎን  በመሆን የተለያዩ ፕሮጀክቶችን በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡

በዚሁ መሰረት ወተርኤድ ኢትዮጵያ ለቢሮ አገልግሎት ሲጠቀምባቸው የነበሩትን የተለያዩ የቢሮ ዕቃዎች እንዲሁም አንድ ያገለገለ መኪና ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ሰስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማማላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡

 1. በጨረታው የሚወዳደሩት ተጫራቾች ኢትዮጵዊ ዜግነት ያላቸው ሆነው ሰነድ ለመውሰድ ሲመጡ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሰነድ ወይም መታወቂያ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 2. በዋተርኤድ ኢትዮጵያ ቢሮ ውስጥ የሚገኙትን ዕቃዎች በአካል በመገኘት የንብረቶቹን ዝርዝር ዋጋ መሙያ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
 3. ተጫራቾች የዕቃውን ዝርዝር ጨረታው ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ቀናት ጠዋት ከ2፡30-6፡30 እና ከሰዓት ከ 7፡30–10፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ዋተርኤድ ቢሮ በመሄድ መመልከት ይችላሉ፡፡
 4. በጨረታው የሚሳተፍ ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ የሚገዛውን ያገለገሉ ዕቃዎች የመነሻ ዋጋ 10 በመቶ /10%/ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ማስያዝ እና ማስገባት ይኖርበታል፡፡
 5. ያገለገሉ ልዩ ልዩ ንብረቶችን የመነሻ ዋጋ 10 በመቶ /10%/ ሲፒኦ ያላስያዘ በሰነዱ የተቀመጡ ሌሎች ነጥቦችን ያላማላ ከጨረታው ውድቅ ይደረጋል፡፡
 6. የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ተኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ4፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪላቸው በተገኙበት በወተርኤድ ቢሮ ይከፈታል፡፡ ሆኖም የመክፈቻው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓላት ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል፡፡ እንዲሁም ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታ በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስተጋጉልም፡፡
 7. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቸቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው በ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ዋጋ በሙሉ መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም ሙሉ ክፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ካልከፈሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለመስሪያ ቤቱ ገቢ ይደረጋል፡፡
 8. አሸናፊ የሆኑ ተጫራቸቾች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው በመክፈል ንብረቶቹን በ10 ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው፡፡
 9. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ ከታች በሚገለፀው አድራሻ መሰረት በመምጣት ወይም በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡
 10. ድርጅቱ /ዋተርኤድ/ ጨረታውን ለመቀበል ወይም ላለመቀበል የሚችል ሲሆን በማናቸውም ጊዜ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 11. ጨረታው ሚያዝያ 22 2014ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት ላይ በዋተርኤድ ቢሮ ይከፈታል፡፡

አድራሻ፡ ቦሌ ክ/ከተማ፤ ወረዳ 03፤ ካሜሩን መንገድ፤ ከኤድናሞል ጎን ሕብረት ኢንሹራንስ ሕንጻ፤ 3ተኛ ወለል ላይ

ስልክ ቁጥር፤ +251 11 669 5965